Skip to main content

መወላወል/ indecision

 


የበሽታዎች ሁሉ በሽታ፤ 

    የስቃዮች በላይ ስቃይ 

የውስጥ ቃጠሎዎች ጌታ፤ 

    የህሊና ግጭቶች አብይ፤

በገዛ አይንህ ክልል ስር፤ 

    በህይወትህ መሃል ድንበር፤

የጉዞህ ውሉ መስመር፤ 

    ሲጠፋህ ርቆ ሲቀበር፤

ቆርጦ ጉዞ ሲቸግር፤ 

    ቆመህ ስትሮጥ፣ ተኝትህም ስትበር፤

ስትወላውል ለመወሰን 

     ባለመወሰንህ ስትወስን፡፡



credit for picture: https://freesvg.org/silhouette-vector-clip-art-of-thinking-guy

Comments