Skip to main content

Posts

Showing posts with the label Economics

አፈንጋጩ ህግ፡ የፍሬደሪክ ባስቲያት ዘ ሎው

  ፍሬደሪክ ባስቲያት መጣጥፉን ሲጀምር ህግ አፈንግጧል ይለናል፡፡ የህግ ተገቢ ቦታው እና አገልግሎቱን ያብራርናል፡፡ ቀጥሎም አፈንግጦ የት እንደደረሰ ያትታል፡፡ በሌላ አባባል የህግ ማፈንገጥ ከየት ወደ የት? ለምንስ? ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጠናል፡፡ መልካም ንባብ፡- ህግ አፈንግጧል! የመንግስት የፖሊስ ኃይልም አብሮ አፈንግጧል! እያልኩ ያለሁት ህግ ተገቢ አላማውን ስቷል ብቻ አይደለም፤ ከዓላማው ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ዓላማን እንዲከተል ተደርጓል ጭምር እንጂ! ህግ የሁሉም አይነት ስግብግብነት መሳሪያ ሆኗል! ወንጀልን መቆጣጠርን ትቶ ህግ እራሱ ሊቀጣቸው ይገቡ የነበሩ ጥፋቶች ወንጀለኛ ነው፡፡ ይህ እውነት ከሆነ፣ ከባድ እውነታ በመሆኑ   አቻዬ ዜጎችን ትኩረት ወደ እዚህ ጉዳይ እንድስብ ምግባር ግድ ይለኛል፡፡ ህይወት ከአምላክ የተሰጠ ስጦታ ነው ከአምላክ ሁሉን ነገር አጠቃሎ የያዘ ስጦታ ተቀብለናል፡፡ ይህ ስጦታ ህይወት ነው - አካላዊ፣ አእምሯዊ እና ምግባራዊ ህይወት፡፡ ሆኖም ህይወት ብቻውን ሊኖር አይችልም፡፡ የህይወት ፈጣሪ እንድንጠብቀው፣ እንድናዳብረው እና እንድናፈፅመው(ፍፅምናን እንድናለብሰው) ኃላፊነት ሰጥቶናል፡፡ ኃላፊነታችንን እንድንወጣ ደግሞ የአስደናቂ ችሎታዎች ስብስብ አቅርቦልናል፡፡ እንዲሁም በተለያዩ አይነት የተፈጥሮ ሃብቶች መሃል አስቀምጦናል፡፡ ችሎታዎቻችንን በመጠቀም እነዚህን የተፈጥሮ ሃብቶች ወደ ምርት ቀይረን እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ህይወት የታሰበላትን መንገድ እንድትጓዝ ይህ ሂደት አስፈላጊ ነው፡፡ ሰው ማለት ህይወት፣ ችሎታ እና ምርት፣ በሌላ አባባል ግለሰባዊነት፣ ነፃነት እና ንብረት ነው፡፡ ብልጣብልጥ የፖለቲካ መሪዎች ማታለያ ምንም ሆነ ምን ሶስቱ የአምላክ ስጦታዎች የትኛውንም ሰብዓዊ ህግ ይቀድማሉ፤ ደ...

የፍሬደሪክ ባስቲያት፤ ዘ ሎው

  መንግስት ሁሉም በሌላው ወጪ ለመኖር የሚጥርበት ታላቅ ልብ ወለድ ነው፡፡                                                                 ፍሬደሪክ ባስቲያት ‹‹ የተጣጣመ ማህበራዊ ህይወትንና የሰው ልጅ ዕድገትን ለመቀዳጀት የሚቻለው ንብረት በግል ሲያዝና ግለሰቦች በኢኮኖሚያዊ እና በሌሎች ዘርፎች ውስጥ ለሚያከናውኑት ተግባር በቂ ነፃነት እና ዋስትና ሲያገኙ ብቻ ነው የሚል …. አስተሳሰብ ነው፡፡›› ሲል ነው የማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላት ለነፃዊነት ወይም ሌበራሊዝም ትርጉም የሰጠው፡፡ ከሞላ ጎደል የአስተሳሰቡን መሰረታዊ አመለካከት ያስቀመጠ ትርጉም ነው፡፡ ነፃዊነት ወይም ሌበራሊዝም ሲነሳ አብረው የሚነሱ በርካታ ምሁራን አሉ፤ ምንአልባት የተወሰኑት   በአንባቢው ምናብ ውልብ ብለው ሊሆን ይችላል፡፡ የዚህ ፅሁፍ አላማ ግን ስለታዋቂዎቹ የነፃዊነት አራማጆች ማውሳት ወይም ስራቸውን ማቅረብ አይደለም፤ ብዙም ስለማይታወቀው ፈረንሳዊ የነፃዊነት አቀንቃኝ ለማውሳት እንጂ፡፡ ዋልተር ኢ. ዊልያምስ የተባሉ ቨርጂንያ የሚገኘው ጆርጅ ማሶን ዩንቨርስቲ የስነ ኢኮኖሚ ፕሮፌሰር እንኳን ስለሰውየው ዘ ሎው የተሰኘ መፅ...