ፍሬደሪክ ባስቲያት መጣጥፉን ሲጀምር ህግ አፈንግጧል ይለናል፡፡ የህግ ተገቢ ቦታው እና አገልግሎቱን ያብራርናል፡፡ ቀጥሎም አፈንግጦ የት እንደደረሰ ያትታል፡፡ በሌላ አባባል የህግ ማፈንገጥ ከየት ወደ የት? ለምንስ? ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጠናል፡፡ መልካም ንባብ፡- ህግ አፈንግጧል! የመንግስት የፖሊስ ኃይልም አብሮ አፈንግጧል! እያልኩ ያለሁት ህግ ተገቢ አላማውን ስቷል ብቻ አይደለም፤ ከዓላማው ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ዓላማን እንዲከተል ተደርጓል ጭምር እንጂ! ህግ የሁሉም አይነት ስግብግብነት መሳሪያ ሆኗል! ወንጀልን መቆጣጠርን ትቶ ህግ እራሱ ሊቀጣቸው ይገቡ የነበሩ ጥፋቶች ወንጀለኛ ነው፡፡ ይህ እውነት ከሆነ፣ ከባድ እውነታ በመሆኑ አቻዬ ዜጎችን ትኩረት ወደ እዚህ ጉዳይ እንድስብ ምግባር ግድ ይለኛል፡፡ ህይወት ከአምላክ የተሰጠ ስጦታ ነው ከአምላክ ሁሉን ነገር አጠቃሎ የያዘ ስጦታ ተቀብለናል፡፡ ይህ ስጦታ ህይወት ነው - አካላዊ፣ አእምሯዊ እና ምግባራዊ ህይወት፡፡ ሆኖም ህይወት ብቻውን ሊኖር አይችልም፡፡ የህይወት ፈጣሪ እንድንጠብቀው፣ እንድናዳብረው እና እንድናፈፅመው(ፍፅምናን እንድናለብሰው) ኃላፊነት ሰጥቶናል፡፡ ኃላፊነታችንን እንድንወጣ ደግሞ የአስደናቂ ችሎታዎች ስብስብ አቅርቦልናል፡፡ እንዲሁም በተለያዩ አይነት የተፈጥሮ ሃብቶች መሃል አስቀምጦናል፡፡ ችሎታዎቻችንን በመጠቀም እነዚህን የተፈጥሮ ሃብቶች ወደ ምርት ቀይረን እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ህይወት የታሰበላትን መንገድ እንድትጓዝ ይህ ሂደት አስፈላጊ ነው፡፡ ሰው ማለት ህይወት፣ ችሎታ እና ምርት፣ በሌላ አባባል ግለሰባዊነት፣ ነፃነት እና ንብረት ነው፡፡ ብልጣብልጥ የፖለቲካ መሪዎች ማታለያ ምንም ሆነ ምን ሶስቱ የአምላክ ስጦታዎች የትኛውንም ሰብዓዊ ህግ ይቀድማሉ፤ ደ...
Legathiopia is a bilingual blog that documents the learning journey of a practicing attorney and host of the Legal Plus podcast. The blog features articles in both English and Amharic, focusing on the Ethiopian legal system and related fields. It serves as a platform for professional discourse, scholarly opinions, and intellectual analysis, aiming to enhance understanding of Ethiopia's legal environment.