For the food by which we live, and for the law by which we live in peace, may Lord make us truly thankful. Ven Thomas Barfett, Lay Sheriff of London’s Chaplain July 1977 የህግ አስፈፃሚ መሆኑን ከስሙ መግለጫ መረዳት የምንችለው ይህ ግለሰብ ለአምላኩ ሲፀልይ ወይም የምስጋና ፀሎቱን እንዴት ብሎ እንደሚያቀርብ ሲገልፅ ነው “በህይወት እንቀጥል ዘንድ ምግብን እንዲሁም በሰላም እንኖርበት ዘንድ ህግን ስለሰጠን ጌታ ከልብ የተመሰገነ ይሁን” በማለት የተናገረው፡፡ ይህ ሰው ህግን ከምግብ ጋር አስተካሎታል፡፡ ደግሞም እውነታ አለው፤ የተረጋጋ ህይወት እንዲኖረን ህግ እና ስርአት የግድ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ለምን? ነጋድራስ ገብረ ህይወት ባይከዳኝ ተናገሩት ተብሎ የሚዘከርላቸው አባባል ወይም ብሂል ምላሹን የያዘ ይመስለኛል፡፡ እንዲህ አሉ፡- “በህግ ከማይኖር ትልቅ ባለብዙ ህዝብና ሠራዊት አገር፣ በህግና ሥርዓት የምትኖር ትንሽ ከተማ ቁም ነገር ትሰራለች፡፡” የህግ ምንነት ተመራማሪ የሆኑት ሮናልድ ዶርኪን Law’s Empire በተባለው መፃሃፋቸው መግቢያ ላይ ህግን ጥሩ አርገው ገልፀውታል፡፡ “We live in and by the law. It makes us what we are: citizens and employees and doctors and spouses and people who own things. It is sword, shield, and menace: we insist on our wage, or refuse to payout rent, or are forced to forfeit penalties, or are closed up in jail, all in the name ...
Legathiopia is a bilingual blog that documents the learning journey of a practicing attorney and host of the Legal Plus podcast. The blog features articles in both English and Amharic, focusing on the Ethiopian legal system and related fields. It serves as a platform for professional discourse, scholarly opinions, and intellectual analysis, aiming to enhance understanding of Ethiopia's legal environment.