Skip to main content

Posts

Showing posts with the label book review

የእስረኞች ዩኒፎርም ነገር እና የማልኮም ግላድዌል Blink – the power of thinking without thinking ነገር

  ማስታወሻ፡ ከተፃፈ የከረመ በወንጀል የተከሰሱ ሰዎች በችሎት ሲቀርቡ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች እስረኞቻቸውን ቢጫ ወይም ቀይ ዩኒፎርም አልብሰው ያቀርቧቸዋል፤ ወደ ፍርድ ቤቶች ያቀና ሰው ሁሉ የሚታዘበው እውነት ነው፡፡ መጀምሪያ ይህን ዩንፎርም የለበሱ እስረኞች ያየሁ ቀን ብዙም ደስ አላለኝም፤ ምን ማለት ነው? ሰው ሳይፈረድበት እንዴት “ወንጀለኛ ነኝ” የሚል መልዕክት የሚያስተላልፍ ባንዲራ አሸክሞ የማምጣት ያህል ባስቀያሚ ቢጫ ወይም ቀይ ዩኒፎርም ችሎት ላይ  ያቀርቧቸዋል? ስል ስብሰለሰል ትዝ ይለኛል፡፡    ስለ ምእራባውያን የወንጀል ችሎቶች አሰብኩ፤ ተከሳሹ ሱፉን ለብሶ ዘንጦ ነው የሚቀርበው፣ ራሱ እምቢኝ አልዘንጥም በቲሸርት እቀርባለሁ ካላለ በስተቀር፡፡ በእኛ ሃገርስ የወንጀል ችሎቶች ለምን እንደዚህ አይደረግም?… ወይ ሱፍ! ጭራሹኑ “ወንጀለኛ ነኝ” ዩኒፎርም አልብሰው ያቀርቧቸዋል፡፡  ማንም ሰው ሳይፈረድበት በፊት እንደወንጀለኛ ሊቆጠር እንደማይገባ የሚደነግገው ህገ መንግስታዊ እና ሰብዐዊ መብታዊ ነፃ ሁኖ የመገመት መብት መርህም በተደጋጋሚ ወደ አዕምሮ ይመላለሳል፡፡ ብዙም ሳልቆይ ግን ለራሴ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ጀመርኩ፡- ያው … ማለት … እ… እ … ባይሆን ጥሩ ነበር፡፡ ለችሎት ሲቀርቡ የራሳቸውን ልብስ ለብሰው ቢቀርቡ የተሻለ ነው፡፡ ግን … ቢለብሱም ያን ያህል ጉዳት የለውም፡፡ በምዕራቡ አለም (የኮመን ሎው የህግ ስርዓት በሚከተሉ አገሮች ) ወንጀለኛ ነው ወይስ አይደለም፣ ጥፋተኛ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ዳኝነት የሚሰጠው የህግ ትምህርት በሌላቸው እማኝ ዳኞች (ጁሪ) ነው፤ በመሆኑም አለባበስ ብሎም አጠቃላይ የተከሳሹ ገፅታ ተፅዕኖ ሊያሳድርባቸው ይችላል፡፡ በእኛ ሃገር ግን ፍርድ የሚሰጠው የህግ ትምህርት እ...