Skip to main content

በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2014 አንዳንድ ድንጋጌዎች ላይ የቀረበ አጭር የመነሻ ሃሳብ ጽሁፍ

በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2014 አንዳንድ ድንጋጌዎች ላይ የቀረበ አጭር የመነሻ ሃሳብ ጽሁፍ



 

   በጠበቃ ዘርኣይ ወልደሰንበት



1. የፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2014 አንቀጽ 63(11) ድንጋጌ መሠረት የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣን የተሰጠው የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ የማውጣት ሥልጣን ነው? ወይንስ የማኅበሩን መመስረቻ ጽሁፍ የማውጣት ሥልጣን ነው?

Article 63(11) of Federal Advocacy Service Licensing and Administration Proclamation No. 1249/2021 stipulated that the General Meeting shall have the power and duty to "Issue the Memorandum of Association of the Association amend and approve same." while its Amharic counterpart says that የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ "የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ ያወጣል፣ ያሻሽላል፣ ያጸድቃል፡፡" በማለት ደንግጓል፡፡ 

በዚህም መሠረት በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2014 አንቀጽ 63(11) ድንጋጌ የእንግሊዝኛው ቅጂ ላይ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የማኅበሩን መመስረቻ ጽሁፍ ያወጣል በሚል በግልጽ የተደነገገ ሲሆን የዚሁ አንቀጽ ድንጋጌ የአማርኛ ቅጂ በበኩሉ ደግሞ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ ያወጣል፡፡" በሚል በግልጽ ተደንግጓል፡፡

ከዚህም አንጻር፣ በአዋጁ አንቀጽ 63(11) ድንጋጌ የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቅጂዎች መካከል ግልጽ የሆነ መሰረታዊ ልዩነት ይገኛል፡፡ እንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ የሕግ አውጪው ትክክለኛ ሀሳብና ፍላጎት ምንም ይሁን ምን የአማርኛው ቅጂ ተፈጻሚነት ይኖረዋል ብሎ ማለፍ አንድ አማራጭ ነው፡፡ ሆኖም በእኔ እይታ ይህ አካሄድ ትክክል አይመስለኝም ብቻ ሳይሆን የሕግ አውጪውን ትክክለኛ ሀሳብና ፍላጎት እሥራ ላይ እንዳይውል የሚያደርግ እና ብርቱ ስንፍና የተጫነው የሕጉን የመዳረሻ ግብ የረሳ፣ ችላ ያለ ወይም ያላገናዘበ ትርጉም የለሽ/ወለፈንዲ (Absurd) የሆነ አቋም መስሎ ይታየኛል፡፡ 

ሕግ አውጪው አካል ውይይት የሚያደርገው የአማርኛው እና የእንግሊዝኛው ቅጂዎች በአንድ ሰነድ ጎን ለጎን ወይም መሳ ለመሳ ሆኖ በሚቀርብለት ረቂቅ አዋጆች ላይ ከመሆኑ አንጻር እና ረቂቅ አዋጆችም በጸደቁ ጊዜም በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው የሚታወጁት  የአማርኛው እና የእንግሊዝኛው ቅጂዎች አብረው በአንድነት በአንድ የነጋሪት ጋዜጣ ከመሆኑ አንጻር ስንመለከተው፣ የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቅጂዎች መካከል ግልጽ የሆነ መሰረታዊ ልዩነት ባጋጠመ ጊዜ ሁሉ የአማርኛው ቅጂ ተፈጻሚነት ይኖረዋል የሚለው አቋም ተገቢነት ያለው አይመስለኝም፡፡ 

እንዲህ አይነት ጉዳዮች በቋንቋ ምንጫ ሳይሆን የሚፈቱት የሕግ አውጪውን ትክክለኛ ሀሳብና ፍላጎት ማዕከል ባደረገ መልኩ ነው፡፡ በተለይም አብዛኛዎቹ ሕጎቻችን ከውጪ ሃገር ሕጎች በሙሉ ወይም በከፊል የሚቀዱ ሲሆን የውጪ ሕጎች/ተሞክሮዎች ወደ አማርኛ ቋንቋ ሲገለበጡ በብዙ ምክንያቶች የተነሳ ግድፈቶች የሚፈጠሩ ሆኖ ሳለ የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቅጂዎች መካከል ግልጽ የሆነ መሰረታዊ ልዩነት ባጋጠመ ጊዜ የአማርኛው ቅጂ ተፈጻሚነት ይኖረዋል ብሎ ማለፍ ተገቢ አይመስለኝም፡፡

በዚህም ምክንያት በማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የማህበሩ የመተዳደሪያ ደንብ በሚል ያረቀቀው ሰነድ ተከልሶ ዳግም ለማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ ውይይት ከመደረጉ በፊት በቅድሚያ የሕግ አውጪውን ትክክለኛ ሀሳብና ፍላጎት የሚያንጸባርቀው የአዋጁ አንቀጽ 63(11) ድንጋጌ የእንግሊዝኛው ቅጂ ነው? ወይንስ የአማርኛው ቅጂ ድንጋጌ ነው? ብሎ መጠየቅና ትክክለኛ ወይም አጥጋቢ የሆነ የተሻለ ሕጋዊ ምላሽ መስጠት ያለበት መስሎ ይታየኛል፡፡ 

በዚህም አግባብ ስንመለከተው፣ በሕግ የተቋቋመ ማኅበር የራሱ የሆነ የመመሥረቻ ጽሑፍ አለው ወይ? ብለን ስንጠይቅ፣ በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ በሕግ የተቋቋመ ማኅበር የራሱ የሆነ የመመሥረቻ ሰነድ ሊኖረው ይችላል፣ በተለይም የሕግ ማዕቀፉ በአስተዳደርና በድርጅታዊ መዋቅር ውስጥ ተጣጣፉነት እንዲኖር የሚፈቅድ ከሆነ።

ነገር ግን በብዙ ሃገራት በሕግ የተቋቋሙ ማኅበራት የተለየ የመመሥረቻ ሰነድ ላይኖራቸው ይችላል። ምክንያቱም መመስረታቸውና የአስተዳደር መርሆቻቸው በፈጠራቸው ሕግ ወይም ደንቦች የተገለጹ ናቸው። ከመመሥረቻው ጽሁፍ/ሰነድ ይልቅ፣ በሕግ የተቋቋሙ ማኅበራት ዓላማቸውን፣ አወቃቀራቸውን እና አሠራራቸውን የሚገልጹ ሌሎች ተመሳሳይ የአስተዳደር ሰነዶች ሊኖራቸው ይችላል። እነዚህ ሰነዶች መመሪያዎችን፣ ቻርተሮችን፣ መተዳደሪያ ደንቦችን፣ ማንዋሎችን ወይም ሕገ ደንቦችን እና ሌሎች ተመሳሳይ ሰነዶችን ሊያካትቱ ይችላሉ።

የሆነዉ ሆኖ በሕግ የተቋቋመ ማኅበር የራሱ የሆነ የመመሥረቻ ሰነድ ይኖረዋል ወይም አይኖረውም የሚለዉ ጉዳይ የሚወሰነው በልዩ የሕግ ማዕቀፎችና በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በሚመለከታቸው ሕጎች ወይም ደንቦች ውስጥ በተገለጹት መስፈርቶች ወይም ድንጋጌዎች ላይ ነው።

በመሆኑም የፌደራል ጠበቆች ማህበር በአዋጅ የተመሰረተ ቢሆንም እንኳ በአዋጅ የተመሰረተ ማህበር የመመስረቻ ጽሁፍ ጨርሶ አያወጣም ሊባል አይችልም፡፡

ስለዚህም የሕግ አውጪውን ሀሳብ የትኛው እንደሆነ ለሕግ አውጪው በመጨረሻ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ጨምሮ ከመጀመሪያው ጀምሮ የተዘጋጁትን ሁሉንም ረቂቅ አዋጆች፣ የረቂቅ አዋጁ አጭር ማብራሪያ ጽሁፍ፣ የአርቃቂዎችም ሆነ የሚኒስቴሮች ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተደረጉ የድምጽ በምስል የተቀዱ ውይይቶች ላይ የተነሱ ሃሳቦችን፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የተደረጉ ውይይቶች ላይ የተነሱ ሃሳቦችን፣ የአዋጁ አንቀጽ 66(2)(c) ድንጋጌ ወይም አዋጁ የተቀዳበትን የውጪ ሃገር ሕግና አተረጓጎምን፣ እና የአዋጁን ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎችን ከወዲሁ በጋራ መርምሮ ትክክለኛ የሆነ ምላሽ ፈልጎ ማስቀመጥ አስፈላጊ መስሎ ይታየኛል፡፡

2. በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2014 አንቀጽ 66(2)(c) ድንጋጌ መሠረት ፕሬዝዳንቱ የሚያዘጋጇቸውን ለማህበሩ አጠቃላይ ሥራዎች አስፈላጊ የሆኑ ረቂቅ መመሪያዎችን የማጽደቅ ሥልጣን ያለው የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ነው ወይንስ የማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ነው?

Article 66(2)(c) of Federal Advocacy Service Licensing and Administration Proclamation No 1249/2021 states that the President shall have the power and duty to "prepare draft Directives necessary for the functions of the Association and implement same when approved by the General Meeting." Pursuant to this provision, it is the general meeting of the Association who has the power to approve draft directives necessary for the general or overall functions of the Association prepared by the president.

However, the Amharic version of Article 66(2)(c) of Federal Advocacy Service Licensing and Administration Proclamation No 1249/2021 states that the President shall have the power and duty to "ለሥራ የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ረቂቅ ያዘጋጃል፣ በሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴው ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል" በማለት ደንግጓል፡፡ በዚህም የአማርኛው ድንጋጌ መሠረት ፕሬዝዳንቱ የሚያዘጋጇቸውን ለማህበሩ አጠቃላይ ሥራዎች አስፈላጊ የሆኑ ረቂቅ መመሪያዎችን የማጽደቅ ሥልጣን ያለው የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ሳይሆን የማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ነው፡፡ በመሆኑም የአዋጁ አንቀጽ 66(2)(c) ድንጋጌ የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቅጂ መካከል መሰረታዊ የሆነ ግልጽ የሆነ ልዩነት አለ፡፡

ከዚህም አንጻር፣ በቅድሚያ የአዋጁ ትክክለኛ ሀሳብና ፍላጎትን የሚያንጸባርቀው የአዋጁ አንቀጽ 66(2)(c) ድንጋጌ የእንግሊዝኛው ቅጂ ነው ወይ? ወይንስ የአማርኛው ቅጂ ድንጋጌ ነው ወይ? ብሎ መጠየቅና የሕግ አውጪውን ሀሳብ የትኛው እንደሆነ ለሕግ አውጪው በመጨረሻ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ጨምሮ ከመጀመሪያው ጀምሮ የተዘጋጁትን ሁሉንም ረቂቅ አዋጆች፣ የረቂቅ አዋጁ አጭር ማብራሪያ ጽሁፍ፣ የአርቃቂዎችም ሆነ የሚኒስቴሮች ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተደረጉ የድምጽ በምስል የተቀዱ ውይይቶች ላይ የተነሱ ሃሳቦችን፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የተደረጉ ውይይቶች ላይ የተነሱ ሃሳቦችን፣ የአዋጁ አንቀጽ 66(2)(c) ድንጋጌ ወይም አዋጁ የተቀዳበትን የውጪ ሃገር ሕግና አተረጓጎምን፣ እና የአዋጁን ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎችን ከወዲሁ በጋራ መርምሮ ትክክለኛ የሆነ ምላሽ ፈልጎ ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው፡፡ 

በሌላ በኩል፣ በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2014 አንቀጽ 66(2)(c) ድንጋጌ መሠረት የማህበሩ ፕሬዝዳንት የተሰጠው ሥልጣን በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 97(2) ድንጋጌ ላይ ማኅበሩ በዚህ አዋጅ የተሰጠውን ሥልጣን እና ተግባራት ለማስፈጸም የሚያስችለውን የሕግ መመሪያ ሊያወጣ ይችላል በሚል ከተመለከተው የሕግ አውጪነት የውክልና ሥልጣን ጋር የተያያዘ ነው ወይን አይደለም? የሚለውን ጥያቄ አንስቶ አብሮ መመርመር ያስፈልጋል፡፡

3. የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2014 አንቀጽ 70(1) ድንጋጌ መሠረት በራሱ ተነሳሽነትም ሆነ ማመልከቻ ሲቀርብለት በአዋጁ አንቀጽ 97(2) መሠረት በማህበሩ የወጡ የሕግ መመሪያዎችን ጨምሮ ማናቸውንም መመሪያዎችን እና ሌሎች ተመሳሳይ ሰነዶችን አይቶ የማጽደቅ፣ የማሻሻል፣ የመለወጥ ወይም የመሻር ውሳኔ ለመስጠት ይችላል ወይ?

የፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2014 አንቀጽ 70(1) ድንጋጌ ላይ የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት አንዱ "በማኅበሩ የሚወሰዱ እርምጃዎችና ውሳኔዎች፤ እንዲሁም በማኅበሩ በሚወጡ መመሪያዎች እና ሌሎች ተመሳሳይ ሠነዶች ሕጋዊነት ላይ ቁጥጥር የማድረግ" እንደሆነ ተደንግጓል፡፡ 

የዚሁ ድንጋጌ የእንግዚዝኛው ቅጂ ደግሞ The Advocates’ Administration Board shall have the power and duty to "Ensure and monitor the legality of measures taken, and decisions passed, by the Association as well as the legality of Directives and other similar documents issued by the Association."

በዚህ ድንጋጌ የአማርኛው ቅጂ ስር "ቁጥጥር የማድረግ" እና በዚሁ ድንጋጌ የእንግሊዝኛው ቅጂ ስር "Ensure and monitor" በሚል የተገለጸው ሥልጣንና ተግባር ምንድን ነው? ቁጥጥር የሚያደርገውስ መቼና እንዴት ነው? ቦርዱ በቁጥጥር ሥራው ወቅት ሕገ ወጥ ነው ብሎ የሚያምነው በማህበሩ የወጣ መመሪያ፣ ውሳኔ ወይም እርምጃ ቢያገኝ ምን እርምጃ ወይም ውሳኔ ለመስጠት ይችላል? በተለይም በማህበሩ የወጡ መመሪያዎችን የማጽደቅ፣ የማሻሻል፣ የመለወጥ ወይም የመሻር ውሳኔ ለመስጠት ይችላል ወይ?

"የመቆጣጠር ሥልጣን" በተለምዶ አንድን የተወሰነ እንቅስቃሴ፣ ሂደት ወይም ሁኔታ የመቆጣጠር ስልጣንን ወይም ችሎታን ያመለክታል። የመቆጣጠር ሥልጣን የተቀመጡ ደረጃዎችን፣ ደንቦችን ወይም አላማዎችን መከታተልን፣ መገምገም እና ማረጋገጥን ያካትታል። ሆኖም ግን "የመቆጣጠር ሥልጣን" የመወሰን ስልጣንን ይሰጣል ወይ? ብለን በምንጠይቅበት ጊዜ፣ የመቆጣጠር ስልጣን ያለው አካል የግድ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን አለው ማለት ላይሆን ይችላል። 

ይልቁንም የመቆጣጠር ስልጣን በመሠረቱ የሚሰጠዉ የመከታተል፣ መረጃ የመሰብሰብ፣ የመተንተን፣ ሪፖርት የማድረግ እና አቅጣጫ የመስጠት ሥልጣን ነዉ። "የመቆጣጠር ሥልጣን" ዓላማው ተገዢነትን፣ ውጤታማነትን እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የታለሙ የተለያዩ ተግባራትን በውስጡ የሚያቅፍ ሥልጣን ነው። ስለዚህም የመወሰን ስልጣን ወይም ውሳኔ የማሳለፍ ኋላፊነት በተለየ አካል የተነጠለ እና የተያዘ ሊሆን ይችላል።  

ነገሩን ይበልጥ ለመረዳት ይረዳ ዘንድ የፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2014 አንቀጽ 70(1) ድንጋጌን ከዚሁ አዋጅ አንቀጽ 70(2) ድንጋጌ እና አንቀጽ 73 ጋር አብሮ በአንድነት በጥንቃቄ አገናዝቦ መመርመር የተሻለ ይመስለኛል። የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ በአዋጁ አንቀጽ 70(1) ድንጋጌ ላይ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን ተሰጥቶት ቢሆን ኖሮ የዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 70(2) ድንጋጌ አስፈላጊ አልነበረም ወይም አይደነገግም ነበር። 

በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 70(2) ድንጋጌ ስር የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ በማኅበሩ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን ተቀበሎ መመርመር እና ውሳኔ መስጠት ሥልጣን የተሰጠው ሲሆን ሆኖም ግን በዚሁ ድንጋጌ ላይ በማህበሩ የወጡ መመሪያዎችን የማጽደቅ፣ የማሻሻል፣ የመለወጥ ወይም የመሻር ውሳኔ የመስጠት ስልጣን እንዳለው አልተገለጸም። 

እንደዚውም የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ በአዋጁ አንቀጽ 70(1) ድንጋጌ ላይ ማናቸውም ውሳኔ የመስጠት ቢሰጠውማ ኖሮ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 73 ላይ ቦርዱ በአዋጁ አንቀጽ 70(1) ድንጋጌ መሠረት በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ይግባኝ የማለት መብት ይደነገግ ነበር። በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 73 ላይ ቦርዱ በአዋጁ አንቀጽ 70(1) ድንጋጌ መሠረት በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ይግባኝ የማለት መብት ያለመደንገጉ የሚያጠናክረው ነገር ቢኖር ቦርዱ በአዋጁ አንቀጽ 70(1) ድንጋጌ ላይ ከመከታተል፣ ከመቆጣጠርና አቅጣጫ ከመስጠት ባለፈ የማጽደቅ፣ የማሻሻል ወይም የመሻር ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን ያልተሰጠው መሆኑን ነው።

በሌላ በኩል፣ it’s essential to examine what constitutes "Directives" and "other similar documents" within the context of Article 70(1) of the same Proclamation? 

When examining what constitutes "Directives" and "other similar documents" within the context of Article 70(1) of the Federal Advocacy Service Licensing and Administration Proclamation No. 1249/2021, it's important to consider whether it includes Articles of Association or Memorandum of Association of the Association within its ambit. 

Directives and other similar documents may encompass various types of guidelines, instructions, manuals, notices, regulations, or administrative documents issued by the Association to govern the operations, functions, and compliance requirements of advocacy services. 

While Articles of Association and Memorandum of Association serve as foundational or supplementary documents for the Association and may contain internal rules and regulations, they may not necessarily fall within the definition of "Directives" or "other similar documents" as specified in Article 70(1). 

If Memorandum of Association and Articles of Association do not fall within the definition of "Directives" or "other similar documents" as specified in Article 70(1) of the Federal Advocacy Service Licensing and Administration Proclamation No. 1249/2021, the Advocates administration board may not have the explicit authority to monitor the legality of such documents. 

If Memorandum of Association and Articles of Association are not considered as falling within the scope of "Directives" or "other similar documents" as specified in Article 70(1) of the Federal Advocacy Service Licensing and Administration Proclamation No. 1249/2021, it suggests that these documents may not necessarily be required to be in compliance with the specific provisions of the Proclamation.

It became clearer when we read it along with Article 99(2) of the Proclamation. The English version of Article 99(2) of the Proclamation states that "Any Proclamation, Regulation, Directive, or practice which is inconsistent with this Proclamation shall not be applicable on matters covered under this Proclamation.” while its Amharic counterpart "ይህን አዋጅ የሚቃረን ማንኛውም አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ ወይም የአሠራር ሥርዓት በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡" በማለት ደንግጓል፡፡ 

Therefore, it seems that especially regarding the memorandum of Association or Articles of Association of the Association there's no primacy of the Federal Advocacy Service Licensing and Administration Proclamation No. 1249/2021 in governing the Federal Advocates' Association.

Comments