የካፒታል ገበያ አዋጅ 1248/2013 ማውጫ
ክፍል አንድ/ PART ONE፡ ጠቅላላ
ድንጋጌዎች/ GENERAL PROVISIONS
1. አጭር ርዕስ/ Short Title
2. ትርጓሜ/
Definition
ክፍል ሁለት/ PART TWO፡ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን/ CAPITAL MARKET AUTHORITY
3. የካፒታል
ገበያ ባለስልጣን መቋቋም/
Establishment of the Capital Market Authority
4. ዋና
መስሪያ ቤት/ Head Office
5. የባለስልጣኑ ዓላማ/ Objective of the Authority
6. የባለስልጣኑ ስልጣን እና ተግባራት/ Powers and Duties of
the Authority
7. የባለስልጣኑ አቋም/ Organisational Structure of
the Authority
8. የቦርድ
አባላት ስብጥር እና አመዳደብ/ Composition and
Appointment of Board of Directors
9. የጥቅም
ግጭት/ Conflicts of Interest
10. የቦርድ
አባላት የሥራ ዘመን/ Tenure of Board Members
11. የቦርድ
አባላት ከሀላፊነት ስለመነሳት ወይም ስለመልቀቅ/ Removal or Resignation of Board
Members
12. የቦርድ
ስልጣን እና ተግባራት/ Powers and Duties of the Board
13. የቦርድ
የስብሰባ ስነ-ሥርዓት/ Meeting Procedures of the Board
14. የዋና
ዳይሬክተር ሹመት፣ ስልጣን እና ተግባራት/ Appointment, Powers, and Duties of Director General
15. ምክትል
ዋና ዳይሬክተር/ Deputy Director General
16. ስልጣን
እና ተግባራት በውክልና ስለመስጠት/ Delegation of
Power and Duties
17. ለባለስልጣኑ መረጃ ስለመስጠ/ Furnishing of Information to the Authority
18. የባለስልጣኑ የገንዘብ ምንጮች/ Funds of the Authority
19. የባለስልጣኑ ሂሳቦች/ Accounts of the Authority
20. የባለስልጣኑን ሂሳቦች በውጭ ኦዲት ለማስመርመር/ External Audit of
the Authority’s Accounts
21. የባለስልጣኑ የበጀት ዓመት/ Financial Year of the
Authority
ክፍል ሶስት/ PART THREE፡ ራሱን በራሱ የሚቆጣጠር ድርጅት እውቅና ስለሚያገኝበት ሁኔታ/ RECOGNITION OF A SELFREGULATORY
ORGANIZATION
22. እውቅና
ለማግኘት ስለሚቀርብ ማመልከቻ/ Application for Recognition
23. ራሱን
በራሱ ለሚቆጣጠር ድርጅት በውክልና የሚሰጥ ሥልጣን
እና ተግባራት ማካተት ስላለባቸው ሁኔታዎች/ Conditions
for Delegation of Power and Duties to a Self-Regulatory Organization
24. የራሱን
በራሱ የሚቆጣጠር ድርጅት ውስጠ-ደንቦች/ Rules of a
Self-Regulatory Organization
25. ውሳኔ
ላይ ስለሚደረግ ገደብ/ Restrictions on Decision
26. የዲሲፕሊን
እርምጃ/ Disciplinary Action
27. የከፍተኛ
ባለሞያ ሹመት እና ለውጥ/ Appointment and Change of Senior
Personnel
28. ከፍተኛ
ባለሞያን ስለማንሳት/ Removal of a Senior Personnel
29. ዓመታዊ
ሪፖርት/ Annual Report
ክፍል አራት/ PART FOUR: የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ/ SECURITIES EXCHANGE
30. ሕገ
ወጥ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን ስለመከልከል/ Prohibition of
Unlawful Securities Exchange
31. የኢትዮጵያ
የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን ስለመመስረት/ Establishment of the Ethiopian
Securities Exchange
32. ሌሎች
የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያዎችና የግብይት መድረኮች/
Other Securities Exchanges and Trading Platforms
33. በሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ገበያና የግብይት መድረኮች ላይ ስለሚወሰደ አስተዳደራዊ እርምጃዎች/ Administrative Measures against a Securities
Exchange and Trading Platforms
34. የሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ገበያ ስራ አመራር/ Management of a Securities Exchange
35. የሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዉስጠ-ደንቦች/ Rules of a Securities Exchange
36. የሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ገበያ ኃላፊነቶች/ Responsibilities of a Securities
Exchange
37. ለባለስልጣኑ መረጃ ስለመስጠት፣ ሪፖርት ስለማድረግ፣ እና እገዛ ስለማድረግ/Information Sharing, Reporting, and Assistance to the
Authority
38. የሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዉስጠ-ደንቦችን ስለማሻሻል/ Amendment to Rules of a Securities Exchange
ክፍል አምስት/ PART FIVE: የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አስቀማጭ እና ክፍያ አጣሪና ፈጻሚ ኩባንያ/ SECURITIES DEPOSITORY AND CLEARING
COMPANY
39. የፈቃድ
አሰጣጥ/ Licensing
40. የሰነደ
ሙዓለ ንዋይ አስቀማጭ እና ክፍያ አጣሪና ፈጻሚ ኩባንያ ግዴታዎች/ Obligations of
Security Depository and Clearing Company
41. ውስጠ-ደንቦችና ውስጣዊ መመሪያዎች/ Rules and Regulations
42. የሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች ምዝገባ/ Securities Registration
43. ስለ
ጥበቃ እና ሪኮርድ አያያዝ/ Custody and Record keeping
44. ክፍያ
እና ርክክብ/ Clearing and Settlement
45. የሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ባለቤትነት መተላለፍ የመጨረሻ ስለመሆኑ/ Finality of Securities Ownership Transfer
46. የሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች አስቀማጭ እና ክፍያ አጣሪና ፈጻሚ ኩባንያ አባሌ መፍረስ ወይም የመክሰር ሥነ ሥርዓት ውስጥ መግባት/ Winding Up or Placement in Bankruptcy Proceeding of a
Securities Depository and Clearing Company Member
47. ሀብት
አጣሪዎች ላይ ተፈጻሚ ስለሚሆኑ ውስጠ-ደንቦችና ስርዓቶች/ Arrangements and Rules
Binding Liquidators
48. ለሰነደ ሙዓለ
ንዋዮች ዝውውር እና ክፍያ ግዴታ የሚሰጥ መያዣ/ Collateral for Securities Transfer and
Settlement Obligation
49. በመዝገብ
የገቡ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን መገበያየት የተከለከለ ስለመሆኑ/ Prohibition in Dealings in
Book-Entry Securities
50. ስለተዋዋይ ወገኖች ስለማሳወቅ/ Reporting on Counterparties
51. ስራን
ስለማስቀጠል እና ከአደጋ ተመልሶ ስለማገገም/ Business Continuity and Disaster
Recovery
52. በሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች አስቀማጭ እና ክፍያ አጣሪና ፈጻሚ ኩባንያ ላይ ስለሚወሰድ አስተዳደራዊ እርምጃ/ Administrative Measures Against a Security Depository
and Clearing Company
53. የመንግስት
ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች/ Government
Securities
54. ልዩ
ስልጣን/ Special Authorization
ክፍል ስድስት/ PART SIX: ለካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ ስለመስጠት/ LICENCING OF CAPITAL MARKET SERVICE PROVIDERS
55. ቁጥጥር
የሚደረግባቸው የካፒታል ገበያ/ Regulated
Capital Market Activities and Services
56. ብቁና
ተገቢ ሰዎች/ Fit and Proper Persons
57. የፈቃድ
ማመልከቻ/ Applications for License
58. የፈቃድ
ወይም የፈቃድ ጥያቄን ስለመከልከል/ Refusal to Grant
or Renew a License
59. ፈቃድን
ስለማገድ/ Suspension of a
License
60. ፈቃድን
ስለመሰረዝ/ Revocation of a
License
61. የራሱን
በራስ ተቆጣጣሪ ድርጅት አባል ስለመሆን/ Membership to a
Self-regulatory Organization
62. የሑሳብ
መዝገብ ቅኝት እና የዉስጥ ቁጥጥር ሥርዓት/ Review of Accounts and Internal Control procedures
63. የዉጭ
ኦዲተሮች ስያሜ/ Appointment of External Auditors
ክፍል ሰባት/ PART SEVEN: የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት/ CAPITAL MARKET TRIBUNAL
64. የካፒታል
ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ስለማቋቋም/ Establishment of the Capital
Market Administrative Tribunal
65. የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ስልጣን/ The Jurisdiction of
the Administrative Tribunal
66. የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ አባላት ሹመት/ Appointment of
Members of the Administrative Tribunal
67. ለአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ አባልነት ብቁ አለመሆን/ Disqualification of Members of the
Administrative Tribunal
68. የአስተዳደራዊ
ፍርድ ቤቱ አስተዳደር/ Administration of
the Administrative Tribunal
69. የአስተዳደራዊ
ፍርድ ቤቱ በጀት እና የሂሳብመዝገብ/ Budget and Accounts of the Administrative Tribunal
70. የአስተዳደራዊ
ፍርድ ቤቱ ዓመታዊ ሪፖርት/ Annual Report of the Administrative Tribunal
71. ይግባኝ
ስለመጠየቅ/ Filing of an
Appeal
72. የአስተዳደራዊ
ፍርድ ቤቱ አሠራር/ Proceedings of the Administrative Tribunal
73. የአስተዳደራዊ
ፍርድ ቤቱ ውሳኔ/ Decision of the Administrative Tribunal
74. ወደ
ፊድራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ስለመጠየቅ/ Appeal to the
Federal High Court
ክፍል ስምንት/ PART EIGHT: ለህዝብ ሽያጭ ማቅረብና የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ግብይት/ PUBLIC OFFERING AND TRADING OF
SECURITIES
75. የሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ምዝገባ/ Registration of Securities
76. በኩባንያዎች
ለሚቀርቡ ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች መግለጫ/ Prospectus for Securities Issued by Companies
77. በቀጣይነት
መረጃን ይፋ የማድረግ ግዴታዎች/ Ongoing Information Disclosure Obligations
78. በሃብት
የተደገፉ ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች አሻሻጥ/ Offer of Asset-Backed Securities
ክፍል ዘጠኝ/ PART NINE: ጥቅምን ይፋ ስለማድረግ/ DISCLOSURE OF INTERESTS
79. ትርጓሜ/
Definition
80. የቀረበ
መረጃ/ Submitted Information
81. ለውጦችን ስለማሳወቅ/ Notification of Changes
82. ይፋ
የማድረጊያ መዝገብ/ Register of Disclosure
ክፍል አስር/ PART TEN: ለቁጥጥር የሚያበቃ የአክስዮን ግዥ እና ስለ አነስተኛ ባለድርሻዎች መብት ጥበቃ / ACQUISITION AND PROTECTION OF
MINORITY INTERESTS
83. ትርጓሜ/
Definition
84. የግዢ
ጥያቄ/ Acquisition Offer
ክፍል አስራ አንድ/ PART ELEVEN: የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድ / COLLECTIVE INVESTMENT SCHEMES
85. የህግ
ቅርጽ/ Legal Form
86. የጋራ
ኢንቨስትመንት ፈንድ አመዘጋገብ/ Registration of Collective Investment Schemes
87. የጋራ
ኢንቨስትመንት ፈንድ ሥራ አከናዋኝ/ Collective Investment Scheme Operator
88. የጋራ
ኢንቨስትመንት ፈንድ ኢንቨስተሮች መብት/ Rights of Collective Investment Scheme Investors
89. የጋራ
ኢንቨስትመንት ፈንድ ኢንቨስትመንት አማካሪ/ Investment Advisor of a Collective Investment
Scheme
90. የጋራ
ኢንቨስትመንት ፈንድ ጠባቂ/ Custodian of Collective Investment Scheme
91. በጋራ
ኢንቨስትመንት ፈንድ ላይ የተጣሉ ገደቦች/ Restrictions on
Collective Investment Schemes
ክፍል አስራ ሁለት/ PART TWELVE: የተከለከሉ የግብይት ተግባራት/ PROHIBITED TRADING PRACTICES
92. ለህዝብ የተሰራጨ መረጃ/ Information Made Public
93. የውስጥ
አዋቂ መረጃ/ Inside Information
94. ውስጥ
አዋቂዎች/ Insiders
95. የውስጥ
አዋቂ ግብይት/ Insider Trading
96. የገበያ
ሸፍጥ/ Market Manipulation
97. የሀሰት
ግብይት/ False Trading
98. የተጭበረበረ
ግብይት/ Fraudulent Transactions
99. የሸፍጥ
ዘዴዎችን መጠቀም/ Use of Manipulative Means
100.
ሀሰተኛ ወይም አሳሳች መግለጫዎች/ False or
Misleading Statements
101.
የጆሮ ጠብ እና ሌሎች የግብይት አይነቶች/ Front–Running and Other Trading Practices
102.
በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግብይት ስለሚጣሉ ገደቦች/ Restrictions on Trading of Securities
ክፍል አስራ ሶስት/ PART THIRTEEN: የካሣ ፈንድ/ COMPENSATION FUND
103.
የካሳ ፈንድ ስለ ማቋቋም/ Establishment of a Compensation Fund
104.
ከፈንድ ስለሚፈጸሙ ክፍያዎች/
Disbursements from the Fund
105.
የፈንድ ሀብትና ዕዳ/ Assets and Liability of the Fund
ክፍል አስራ አራት/ PART FOURTEEN: ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች/ MISCLLANEOUS PROVISIONS
106.
የወንጀል ተጠያቂነት/ Criminal Liability
107.
አስተዳደራዊ እርምጃዎች/
Administrative Measures
108.
ደንብ እና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን/
Power to Issue Regulations and Directives
109.
የፈቃድ ዕድሳት/ License Renewal
110.
የሠራተኞች አስተዳደር/ Administration of
Employees
111.
አለመግባባቶችን ስለመፍታት/ Settlement of Disputes
112.
ስለተሻሩና ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ህጎች
Inapplicable Laws
113.
አዋጁ የሚጸናበት ቀን/ Effective Date
የካፒታል ገበያ አዋጅ 1248/2013 የቃላት ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡-
1. “Advertisement” / ‹‹ማስታወቂያ›› ማለት፦
ሀ) በጽሁፍ፣
ማስታወቂያ በመለጠፍ፣ ወይም በሰርኩላር ወይም በሌሎች
ሰነድች፤
ለ) በፎቶግራፎች፣ በሲኒማቶግራፊ ፊልሞች ወይም ቪዲዮ አውደ-ርዕይ፤
ሐ) በድምጽ
ስርጭት፣ በቴሌቪዥን፣ ወይም ቀረጻዎችን በማሰራጨት፤ ወይም
መ) እንደ ድረ-ገጽ እና ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ባሉ ሌሎች ኤሌክትሮኒክ
የመገናኛ ብዙሃን መድረኮች፤ የሚተላለፉ ማስታወቂያዎችን ያካትታል፤
2. “An Appointed Representative” / ‹‹ተሿሚ እንደራሴ›› ማለት በባለስልጣኑ የንግድ ፈቃድ የተሰጠውን የካፒታል
ገበያ አገልግሎት ሰጪ በመወከል ቁጥጥር የሚደረግባቸውን ተግባራት የሚያከናውን ሰው ነው፤
3. “Asset-Backed Securities (ABS)”/ ‹‹በሃብት የተደገፉ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች›› ማለት የሚከተሉትን ያካትታል፡-
ሀ) ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች ሆነው የሚያስገኙት የገንዘብ ፍሰት በዋናነት ተለይተው በሚታወቁ የተሰብሳቢ ወይም ሌሎች የገንዘብ ሰነድች፣ ቋሚ
ወይም ተዘዋዋሪ የሆኑ፣ በውል በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ ገንዘብ የሚለወጡ፣ በተጨማሪም እነዚህን ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች ለያዛቸው ሰው የሚከፈለው ገንዘብ በወቅቱ እንዲፈፀም ለማረጋገጥ ዋስትና የተደረጉ ማንኛውም መብቶች ወይም ሌሎች ሃብቶች፣
ለ) አክሲዬኖችን ወይም ከጋራ የኢንቨስትመንት ፈንድች የሚገኙ መብቶችን ሳይጨምር ነገር ግን
የተስፋ ወረቀቶችን ጨምሮ ማንኛውም ሰነደ ሙዓለ ንዋይ፣
ሐ) ሊሸጡ
እና ሊለወጡ የማይችሉ ሰነድችን ሰብስቦ እንዲሸጡ
እንዲለወጡ ወይም በራሳቸው ለግብይት የማይውሉ ሰነድች የግብይት ሰነደ
ሙዓለ ንዋይ መፍጠር ሂደትን ተከትሎ በተቋቋመ ባለ ልዩ ተልዕኮ ተቋም ሃብት ላይ
ከሚጠራቀም ዋና ብድር ወይም ወለድ፣ ገቢ፣ የካፒታል ክፍፍል ወይም
ክፍያዎች ወይም በእነዚህ ተቋማት ላይ ድርሻ የያዙ ባለሃብቶች ማንኛውም መብት ወይም ጥቅም፣ የዕዳ ሰነድ ወይም ህጋዊ የአላባ ተጠቃሚነት ወይም በድርሻ
ላይ የጥቅም መብቶችን የሚያረጋግጡ የምስከር ወረቀቶች፣ ወይም
መ) ሌላ
ማንኛውም በሀብት የተደገፈ ሰነደ
ሙዓለ ነዋይ አይነት መብት፣ ጥቅም ወይም ሰነድ፤
4. “Bank” / ‹‹ባንክ›› ማለት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ስራ እንዲሰራ ፈቃድ የተሰጠው
ኩባንያ ወይም በመንግስት ባለቤትነት ስር ያለ
ባንክ ማለት ነው፤
5. “Capital Market” / ‹‹የካፒታል ገበያ›› ማለት እንደ አክሲዮን፣ ቦንድ፣ ተዛማጅ ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች ወይም እነዚህን የመሰሉ የተለያዩ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግብይት የሚደረግበት ገበያ ነው፤
6. “Capital Market Participants / ‹‹የካፒታል ገበያ
ተዋናዮች›› ማለት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች፣
የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጪዎች፣ ኢንቨስተሮች፣
የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ፣ ተገቢነት ያላቸዉን
ዉልች ያደረጉ ብቁ የሆኑ ተጓዳኝ ወገኖች እና
የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች አስቀማጭ እና ክፍያ አጣሪና
ፈጻሚ ኩባንያዎች ናቸው፤
7. “Capital Market Service Provider” / ‹‹የካፒታል
ገበያ አገልግሎት ሰጪ›› ማለት ማንኛውም በዚህ አዋጅ መሠረት
ቁጥጥር በሚደረግባቸው የካፒታል ገበያ ስራዎች ላይ የተሰማራ
ሰው ነው፤
8. “Central Clearing Counterparty”/ ‹‹ማዕከላዊ
የክፍያ አጣሪና ፈጻሚ ወገን›› ማለት፦
ሀ) በሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ግብይቶች ላይ ድህረ ግብይት የማጣራት እና ክፍያ የመፈጸም ስራን፣ እና
ለ) በሰነደ ሙዓለ
ንዋይ ተገበያዮች መካከል የተቃራኒ ወገን ስጋትን የመውሰድ ስራን የሚመለከት ነው፤
9. “Central Securities Depository” / ‹‹ማዕከላዊ
የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት›› ማለት፡-
ሀ) ከተማከለ
የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አያያዝ ጋር በተገናኘ፡-
(፩) ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች ወጥነት ባለው መንገድ የሚከማቹበት፣ ወይም ወደ ኤሌክተሮኒክ ይዘት ተቀይረው የሚቀመጡበት፣
ወይም ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች በአውጪው ኩባንያ ወይም
በአውጪው ኩባንያ ስም ሆኖ በሚሰራ ሌላ ኩባንያ ስም የሚመዘገቡበት ሆኖ እነዚህ ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮችን በተመለከተ የሚደረግ ግብይት ሰነድቹን በአካል ማረካከብ
ሳያስፈልግ የሰነድቹ መተሳሰቢያ መዝገብ ላይ ብቻ በሚደረግ ወጪና ገቢ ለማስተላለፍ የሚያስችል ስርዓት፣ ወይም
(፪) በሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች ግብይት ሂደት ወቅት የሰነደ ሙዓለ
ንዋዮችን ምዝገባ፣ ክፍያና እና ርክክብ ያለ አካላዊ ቅብብል ለማከናወን የሚያስችል ወይም ግብይቱን የሚያሳልጥ ዘዴ ወይም ስርዓት፤
እና
ለ) ሌሎች ተያያዥ የሆኑ ድጋፎችን ወይም አገልግሎቶችን የሚሰጥ ስርዓት ነው፤
10. “Close-Out Netting’’/ ‹‹የመዝጊያ ማቻቻያ›› ማለት በሁለት ሰዎች መካከል በተደረገ ስምምነት ዉስጥ ያሉ የተወሰኑ ድንጋጌዎችን ተፈጻሚ ማድረግ ሆኖ፦
ሀ) ሌላኛውን
ወገን በተመለከተ ግዴታን ባለመወጣት የሚከሰት ሁኔታ ወይም ሌላ የውል ማቋረጫ ሁኔታ ሲያጋጥም
ወይም በውሉ በተመለከተው መሰረት በአንዳንድ ሁኔታዎች ወዲያውኑ
ሊከሰት ወይም አንደ ሰው ለሌላው ሰው በሚሰጠው ማስጠንቀቂያ ሊጀመር
የሚችል፤እና
ለ) የሚከተለው ውጤት ሲኖረው፤
(፩) ከአንድ
ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ወይም ግንኙነት እና ተገቢነት ባላቸው ውሎች ላይ በሚነሱ ወይም በተያያዙ ማናቸውም አሁን ወይም ወደፊት የሚከፈሉ ክፍያዎች ወይም የማስረከብ መብቶች ወይም ግዴታዎች
ሲቋረጡ፣ ሲጣሩ እና / ወይም ሲፋጠኑ፤
(፪) በዚህ
ንዐስ አንቀጽ ፊደል ተራ ለ(፩) መሰረት የተቋረጠን፤ ሂሳቡ
የተጣራን ወይም የተፋጠነን እያንዳንድን መብትና ግዴታ ወይም የመብቶችና ግዴታዎች መደብን በተመለከተ የመዝጊያ ዋጋ ፤ የገበያ ዋጋ፤ የማጣሪያ ዋጋ ወይም ምትክ ዋጋ ስሌት ወይም ግምት እና እያንዳንዱን
ዋጋ ወደ አንድ አይነት መገበያያ ገንዘብ ሲለወጥ፤
(፫) አንድ
ሰው የተጣራውን ሂሳብ መጠን የሚያህል ክፍያ ለሌላ ሰው እንዲፈጽም ግዴታ የሚጥል በዚህ ንዐስ አንቀጽ ፊደል ተራ ለ(፪) መሰረት የተሰላን የተጣራ
ዕዳን /ሂሳብን/ የመክፈል ግዴታን በማቻቻል ወይም በሌላ መንገድ መወሰን ነው፤
11. “Collective Investment Scheme”/ ‹‹የጋራ የኢንቨስትመንት
ፈንድ›› ማለት፦
ሀ) ሰዎች
ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ወይም ሌሎች ንብረቶችን
በባለቤትነት በመያዝ፣ በይዞታ በማቆየት፣ በማስተዳደር፣ ወይም በማስተላለፍ ገቢ ወይም ትርፍ ለማግኘት የሚሳተፉበት ወይም ይህን ዓይነት ዓላማ ወይም ውጤት ለማስገኘት ታስቦ የተቋቋመ ወይም ከእንደዚህ ዓይነት አሰራር ከሚገኝ ገቢ ወይም ትርፍ የሚከፈልበት የስምምነት
መዋቅር፤
ለ) በስምምነት መዋቅሩ ውስጥ የሚሳተፉ ኢንቨስተሮች የጋራ ማዕቀፉ ሀብቶች የዕለት- ተለት አስተዳደር ቁጥጥር የማይዙበት፤ እና
ሐ) የፈንድን
ሀብቶች የሚያስተዳድረው ሰው የፈንድን ሀብት እና የአባላቱን ሂሳቦች በኃላፊነት የሚያስተዳድርበት ነው፤
12. “Collective Investment Scheme Operator”/
‹‹የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድ ስራ አከናዋኝ›› ማለት ለአንድ የጋራ የኢንቨስትመንት ፈንድ የስራ
አመራር እና አፈጻጸም አጠቃላይ ኃላፊነት ያለበት ተቋም ነው፤
13. “Company”/ ‹‹ኩባንያ›› ማለት በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ መሠረት የተቋቋመ የአክሲዮን ኩባንያ
ነው፤
14. “Credit Rating Service”/ ‹‹ብድር የመመለስ ብቃት ምዘና አገልግሎት›› ማለት የአንድን ተቋም፣ ሰነደ ሙዓለ
ንዋይ፣ ወይም የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጭ ብድርን የመመለስ አቅም በተመለከተ ተቀባይነት ያላቸው እና የታወቁ የመመዘኛ መስፈርቶችን በመጠቀም
የሚሰጥ አስተያየት ነው፤
15. “Credit Rating Service Agency”/ ‹‹ብድር የመመለስ ብቃት ምዘና አገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲ›› ማለት በዚህ አዋጅ መሰረት በተሰጠ የባለስልጣኑ ፈቃድ ብድር የመመለስ ብቃት ምዘና አገልግሎት የሚሰጥ ሰዉ ነዉ፤
16. “Custodian”/ ‹‹ጠባቂ›› ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት የደንበኞችን ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮች ለጥበቃ ዓላማ ወይም ለምቹ አያያዝ ሲባል በይዞታው ስር የሚያስቀመጥ የገንዘብ ተቋም
ነው፤
17. “Days”/ ‹‹ቀናት›› ማለት በኢትዮጵያ ካላንደር መሠረት ከቅዳሜ፣ ከእሁድ እና ከሕዝብ በዓላት ውጭ ያሉ ቀናት
ማለት ነው፤
18.“Dealing in Securities”/ ‹‹በሰነደ ሙዓለ ንዋይ መገበያየት›› ማለት ለራስ ወይም ስለ ሌሎች ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮችን፡-
ሀ) መሸጥ
ወይም መግዛት፣
ለ) ማውጣት ወይም ለሽያጭ ማቅረብ፣
ሐ) ማስቀመጥና
መጠበቅ፣
መ) ክፍያ
ማጣራትና መፈጸም፤
ሠ) ማበደር ወይም ማስያዝ፣ ወይም
ረ) ሌላ
ማንኛውም ባለስልጣኑ በሰነደ
ሙዓለ ንዋይ የሚደረግ ግብይት ነው ብሎ የሚወስነው ስራ ነው፤
19. “Debt Security”/ ‹‹የብድር ሰነደ ሙዓለ ንዋይ›› ማለት ማንኛውም በኩባንያ የሚወጣ ወይም ሊወጣ የታቀደ
የዕዳ ሰነድ፣ ዋስትና ያለው የዕዳ ሰነድ፣ የብድር ስቶክ፣
ቦንድ፣ ወይም የተስፋ ሰነድ ሆኖ ባለዕዳነትን የሚፈጥር ወይም የሚያረጋግጥ ነው፤
20. “Dematerialisation"/ ‹‹ግዐዝ-አልባ ማድረግ›› ማለት ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮችን በኤሌክትሮኒክ መንገድ ማውጣት እና መመዝገብ ነው፤
21. “Dematerialised Security”/ ‹‹ግዐዝ-አልባ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ›› ማለት የሰነደ ባለቤትነት በኤሌክትሮኒክ የምዝገባ ደብተር ባለቤትነትን በማስገባት ብቻ የሚረጋገጥበት ሰነደ ሙዓለ
ንዋይ ነው፤
22. “Derivatives” or “Derivatives Contract”/
‹‹ተዛማጅ›› ወይም ‹‹ተዛማጅ ውል›› ማለት ዋጋው ከሌላ መሠረታዊ ከሆነ እንደ አክሲዮን፣ ቦንድ፣ ወይም ምርቶች
እና ገንዘቦች ያሉ ሀብቶች ወይም ምጣኔዎች የሚመነጭ ሆኖ እንደ አክሲዮን ወይም ሌላ የገንዘብ
ሰነድ የሚሸጥ፣ የሚገዛ ወይም ግብይት የሚደረግበት ገንዘብ ነክ ሰነድ ነው፤
23. “Derivatives Exchange”/ ‹‹የተዛማጅ ውሎች ገበያ››
ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት በገበያው ተመዝግበው ግብይት ሊደረግባቸው የሚችሉ ተዛማጅ ውሎች እንዲመዘገቡበት በባለስልጣኑ ፈቃድ የተሰጠው ወይም ለዚሁ ዓላማ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጡ ደንቦች እና መመሪያዎች መሠረት ይሁንታ የተሰጠው ገበያ ነው፤
24. “Eligible Contract”/ ‹‹ተገቢነት ያለው ውል›› ማለት ተዛማጅ ውል፣ መልሶ የመግዛት ውል ወይም ባለስለጣኑ በመመሪያ ተገቢነት ያለው ብሎ የሚወስነው ሌላ ግብይት ነው፤
25. “External Auditor”/ ‹‹የውጭ ኦዲተር›› ማለት የኦዲት አገልግሎት እንዲሰጥ በሚመለከተው የመንግስት አካል ፈቃድ የተሰጠው ገለልተኛ ኦዲተር ነው፤
26. “False Statement”/ ‹‹ሀሰተኛ መረጃ›› ማለት በአቀራረቡ እና በተገለጸበት አውድ ውስጥ ሲታይ አሳሳች የሆነ አገላለጽ ሲሆን በደንበኛ ሳቢ መግለጫ ውስጥ ሳይካተት የቀረ ወይም ሆን ተብሎ ኢንቨስተሮችን ወይም የገበያ ተሳታፊዎችን ለማሳሳት የተገለጸን ማንኛውም በጽሁፍ የቀረበ ነገርን ይጨምራል፤
27. “Financial Instruments”/ ‹‹የገንዘብ ሰነድች›› ማለት በተዋዋዮች መካከል የሚደረጉ፣ የሚሻሻሉ፣ ግብይት እና ክፍያ የሚደረግባቸው ገንዘባዊ ይዘት ያላቸው ውሎች ናቸው፤
28. “Foreign Investor”/ ‹‹የውጭ አገር ኢንቬስተር›› ማለት እንደ ኢትዮጵያዊ መቆጠር የሚፈልግ ትውልደ
ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር ዜጋን ሳይጨምር በኢትዮጵያ ውስጥ የውጭ አገር ካፒታል በስራ ላይ ያዋለ
ሆኖ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡-
ሀ) የውጭ
አገር ዜጋ፤
ለ) የውጭ አገር ዜጋ የባለቤትነት ድርሻ የያዘበት ድርጅት፤
ሐ) ከኢትዮጵያ
ውጭ በማንኛውም ኢንቬስተር የተመዘገበ ድርጅት፤
መ) በ
‹ሀ›፣ ‹ለ› እና ‹ሐ› ከተጠቀሱት ኢንቬስተሮች በሁለቱ ወይም በሦሥቱ በጋራ የተቋቋመ ድርጅት፤ ወይም
ሠ) እንደ
ውጭ አገር ኢንቬስተር መስተናገድ የመረጠ በቋሚነት በውጭ አገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ፤
29.“Government”/ ‹‹መንግስት›› ማለት የኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ነው፤
30. “Immobilization”/ ‹‹ሰነድን ማስቀመጥ›› ማለት በወረቀት መልክ ያለን የሰነደ ሙዓለ
ንዋዮችን የምስክር ወረቀቶች በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ
ንዋዮች ግምጃ ቤት በማስቀመጥ የሰነድቹ ዝውውር በሂሳብ መዝገብ ለውጥ ብቻ እንዲከናወን ማስቻል ነው፤
31. “Immobilized Security”/ ‹‹ተቀማጭ የተደረገ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ›› ማለት የመሠረታዊው ሰነደ ሙዓለ
ንዋይ የምስክር ወረቀት በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት እንዲመዘገብና
እንዲቀመጥ የተደረገ ሰነድ ነው፤
32. “Initial Public Offering”/ ‹‹የመጀመሪያ ዙር የሕዝብ
ሽያጭ›› ማለት:-
ሀ) አስቀድሞ
የኩባንያው ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ለሕዝብ በሽያጭ ባልቀረቡበት ሁኔታ፤ ወይም
ለ) አስቀድሞ ለህዝብ በሽያጭ የቀረቡት የኩባንያው አክሲዮኖች ከጊዜ በኋላ ሙሉ በሙሉ በኩባንያው ተመልሰው በተገዙበት
ሁኔታ፣ ማንኛውንም የአንድ ኩባንያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ለሕዝብ ለመሸጥ ማቅረብ ነው፤
33. “Investor”/ ‹‹ኢንቨስተር›› ማለት ትርፍ ለማግኘት ሲል በዚህ አዋጅ መሰረት ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮችን የሚገዛ፣ የሚሸጥ ወይም የሚይዝ ማንኛዉም ሰዉ ነዉ፡፡
34. “Investment Bank”/ ‹‹የኢንቨስትመንት ባንክ›› ማለት ተቀማጭ ገንዘብ የማይሰበስብ የገንዘብ ተቋም ሆኖ በሌሎች
ኩባንያዎች፣ በመንግስት ወይም በሌላ ተቋም የሚሸጡ ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮችን በውክልና በመሸጥ ወይም ሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጪውን ከገዢ ሕብረተሰብ
ጋር በማገናኘት ካፒታል በማሰባሰብ፣ የኩባንያዎችን ውህደት እና ዳግም መልሶ የማዋቀር ስራዎችን በማገዝ፣ ለደንበኞቹ እንደ ደላላ እና ገንዘብ ነክ በሆኑ ጉዳዮች የአማካሪነት አገልግሎት የሚሰጥ
ተቋም ነው፤
35. “Investment”/ ‹‹ኢንቨስትመንት›› ማለት ቀጥለው የተዘረዘሩትን ያካትታል፡-
ሀ) ለህዘብ በሽያጭ የቀረቡ ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች፣
ለ) በውጭ አገር የሰነደ ሙዓለ
ንዋዮች ገበያ ወይም የግብይት መድረክ የተመዘገቡ ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮች፣
ሐ) በዚህ
አዋጅ መሠረት በተፈቀደ የጋራ የኢንቨስትመንት ፈንድ ውስጥ ያለ
የባለቤትነት ድርሻ ወይም ክፍልፋይ፣
መ) ከላይ
የተጠቀሱ ዓይነት የባለቤትነት ድርሻዎችን ወይም ክፍልፋዮችን
እና ሌሎች መሰል ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለመግዛት የተመደቡ ገንዘቦች፣ ወይም
ሠ) ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም በባለስልጣኑ በሚወጣ መመሪያ ኢንቨስትመንት ነው ተብሎ የተፈረጀ ሌላ ማንኛውም
ሰነደ ሙዓለ ንዋይን፡፡
36. “Investment Adviser”/ ‹‹የኢንቨስትመንት አማካሪ›› ማለት ፈቃድ ተሰጥቶት እና:-
ሀ) ኢንቨስትመንትን
በተመለከተ ሌሎችን የማማከር ስራ የሚሰራ፤
ለ) ኢንቨስትመንትን የተመለከቱ ሪፖርቶችን እና ትንተናዎችን የማውጣት እና የማሰራጨት ስራን መደበኛ ስራው አድርጎ የሚሰራ፤ ወይም
ሐ) እንደ
ቦንድ፣ ምርት፣ የጋርዮሽ ገንዘብ እና አክሲዮን በመሳሰሉ የተወሰኑ የኢንቨስትመንት ዓይነቶች ላይ የተለየ ፈቃድ ተሰጥቶት በገንዘብ ነክ እና በኢንቨስትመንት ጉዳዮች
ላይ ምክር የሚሰጥ ሰው ነው፡፡
37. “Issuer” / ‹‹አውጪ›› ማለት መንግስት፣ ኩባንያ ወይም ሌላ ሕጋዊ ድርጅትን ጨምሮ ማንኛውንም
ሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለሽያጭ የሚያወጣ፣ ወይም ለማውጣት መዘጋጀቱን የሚያስተዋውቅ ሰው ነው፤
38. “License”/ ‹‹ፈቃድ›› ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት ባለስልጣኑ ለአንድ ሰው በማንኛውም ባለስልጣኑ በሚቆጣጠረው ዘርፍ ላይ እንዲሰማራ የሚሰጠው የንግድ ፈቃድ ነው፤
39. “Licensed Securities Exchange”/ ‹‹ፈቃድ ያለው የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ›› ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት ፈቃድ የተሰጠው የሰነደ ሙዓለ
ንዋዮች ገበያ ነው፤
40. “Listing Requirements”/ ‹‹የምዝገባ መስፈርቶች›› ማለት የሰነደ ሙዓለ
ንዋዮችን ገበያ በተመለከተ የሚከተሉት ጉዳዮች የሚገዙበት
ውስጠ-ደንብ ነው፡-
ሀ) በሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ገበያ ላይ ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮችን ለመመዝገብ ወይም ለሽያጭ እንዲቀርቡ የመፍቀድ አሰራር፣ ወይም ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮችን ከምዝገባ ለመሰረዝ ወይም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች፤ ወይም
ለ) በመዝገቡ ውስጥ ስለገቡ አውጪዎች ወይም ሌሎች በመዝገብ እንዲገቡ ስለተፈቀደላቸው ሰዎች አሰራር ወይም ስነምግባር በሚመለከት የሚወጡ ውስጠ- ደንቦች ሆነው፤
(፩) በሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ገበያው የወጡ ወይም በሰነደ ሙዓለ
ንዋይ ገበያው መሠረታዊ ሰነድች የተካተቱ፤ ወይም
(፪) በሌላ
ሰው ወጥተው በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያው በሥራ ላይ የዋሉ፡፡
41. “Listed Securities”/ ‹‹የተመዘገቡ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች›› ማለት ፈቃድ ባለው የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ላይ የተመዘገቡ
ወይም ለሽያጭ የቀረቡ ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች ማለት ነው፤
42. “Market Maker”/ ‹‹ገበያ ከፋች›› ማለት ባለስልጣኑ ተግባራዊ በሚያደርገው የቁጥጥር ስርዓት መሠረት ለአንድ ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች አቅርቦት እና ፍላጎት
እንዲኖር የሚያደርግ ሰው ነው፤
43. “Mark the close”/ ‹‹ከፍ አድርጎ መዝጋት›› ማለት ሆን ብሎ የሰነደ
ሙዓለ ንዋዩን የመዝጊያ ዋጋ ከፍ ለማድረግ በማሰብ ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮችን በእለቱ የግብይት ማብቂያ የመጨረሻ ሰዓት
ላይ ገበያው ላይ ካለው ዋጋ እጅግ ከፍ ባለ
ዋጋ መግዛት ነው፤
44. “Mutual Fund”/ ‹‹የጋርዮሽ ገንዘብ›› ማለት ከኢንቨስተሮች ገንዘብን የማሰባሰብ እና የኢንቨስትመንት ስጋቶችን
የመጋራት ዓላማ ወይም ውጤት ያለውና ትርፍ እዲከፋፈሉ፣ ወይም ኢንቨስትመንቶቹን
ከመግዛት፣ ከመያዝ፣ ከማሰተዳደር እና ከማስተላለፍ የሚገኙ ጥቅሞችን በጋርዮሽ ገንዘቡ ለሚሳተፉ ኢንቨስተሮች የሚያስገኙ የባለቤትነት ድርሻዎችን ወይም ክፍልፋዮችን የሚሸጥ ኩባንያ ወይም ሽርክና
ማህበር ነው፤
45. “National Bank” / ‹‹ብሔራዊ ባንክ›› ማለት በተሻሻለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፭፻፺፩/፪ሺ (591/2008) መሠረት የተቋቋመው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው፤
46. “Commensurable Agreement”/ ‹‹የማቻቻያ ስምምነት››
ማለት ስለማቻቻል የሚደነግግ በሁለት ሰዎች መካከል የተደረገ ስምምነት ሆኖ ያለምንም ገደብ:-
ሀ) ከሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ የማቻቻያ ስምምነቶች መሰረት ክፍያቸው
የደረሰ ገንዘብን የሚያቻችል ስምምነትን፤
እና
ለ) ከማቻቻያ ስምምነት ጋር ተያያዥ ወይም የስምምነቱ አካል የሆነ የዋስትና አደረጃጀትን ያካትታል፡፡
47. “Nominee”/ ‹‹የተውሶ ስም›› ማለት አንድ ሰው ከሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ባለቤት ጋር ባደረገው ሰነደ
ሙዓለ ንዋይ የመጠበቅ ስምምነት መሠረት ሰነደ በስሙ በገቢና ወጪ መዝገብ ውስጥ የተመዘገበ ሆኖ
የሰነደ ባለቤትና ተጠቃሚ ሌላ ሰው የሆነበት አሰራር
ነው፤
48. “Over-the-Counter Market”/ ‹‹ያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያ›› ማለት ዕውቅና ከተሰጠው የሰነደ ሙዓለ
ንዋይ ገበያ ውጭ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች እና/ወይም ተዛማጆች በሻጮችና
በገዢዎች መካከል በቀጥታ (ፊት ለፊት ወይም እንደ
ስልክ እና የኮምፒዩተር መረብ) በሚደረግ ግንኙነት ግብይት የሚደረግበት ገበያ ነው፤
49. “Primary Market”/ ‹‹የመጀመሪያ ደረጃ ገበያ›› ማለት በውክልና ሻጮች አስተባባሪነት አዳዲስ አክሲዮኖችን፣ ቦንድችን፣ የተስፋ ሰነድችን፣ እና ሌሎች ገንዘባዊ
ሰነድችን በመሸጥ አዲስ ካፒታል የሚሰበሰብባቸው ገበያ ናቸው፤
50. “Primary Regulator”/ ‹‹የመጀመሪያ ደረጃ ተቆጣጣሪ›› ማለት ቁጥጥር በሚደረግባቸዉ ተግባራት ላይ ተቀዳሚ የመቆጣጠር እና በበላይነት የመከታተል ስልጣን ያለው የፌዴራል መንግስት ኤጄንሲ ነው፤
51. “Private Placement”/ ‹‹ለግል ሽያጭ ማቅረብ›› ማለት ባለስልጣኑ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮችን ለሕዝብ ሳያቀርቡ አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ኢንቬስተሮች ማቅረብ ነው፤
52. “Prospectus”/ ‹‹ደንበኛ ሳቢ መግለጫ›› ማለት በአክሲዮን ኩባንያ ወይም በኩባንያው ስም የወጣ እና ኩባንያው
ስላወጣቸው አክሲዮኖች፣ የዕዳ ሰነድች፣ ወይም ሌሎች የኩባንያው ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮች ባህሪ፣ እና ዓላማ የሚገልጹ መረጃዎችን በማካተት ሕዝብ እንዲገዛ ጥሪ የሚደረግበት የጽሁፍ ሰነድ ወይም ሕትመት ነው፤
53. “Public Company”/ ‹‹የሕዝብ ኩባንያ›› ማለት ሰነድቹ በሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ገበያ ቢመዘገቡም ባይመዘገቡም አክሲዮኖቹ በሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ገበያ ወይም ባልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያ የሚሸጡ
የአክሲዮን ኩባንያ ነው፤
54. “Public Debt Security”/ ‹‹የህዝብ የብድር ሰነደ ሙዓለ ንዋይ›› ማለት በመንግስት ወይም በመንግስት ስም ወይም በመንግስት ተቋማት
ስም የሚወጣ ባለዕዳነትን የሚፈጥር ወይም የሚያረጋግጥ ማንኛውም
የብድር ስቶክ፣ ቦንድ፣ የተስፋ ሰነድ፣ ወይም ሌላ መሰል ሰነድ ነው፤
55. “Public Enterprise”/ ‹‹የመንግስት የልማት ድርጅት›› ማለት ሙሉ በሙሉ በመንግስት ባለቤትነት የተያዘ ድርጅት ነው፤
56. “Public Offer”/ ‹‹ለሕዝብ ማቅረብ›› ማለት አንድ ኩባንያ በንግድ መዝገብ ከመመዝገቡ ወይም አውጪው ኩባንያ ሰነድቹን ከመሸጡ በፊት ካፒታሉን
ለማሰባሰብ በአደራጆቹ አማካኝነት የሚደረግ ሰነድቹን ለሕዝብ ለሽያጭ የማቅረብ ተግባር ነው፤
57. “Publicly Traded Security”/ ‹‹ለሕዝብ የሚሸጥ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ›› ማለት በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ወይም ባልተማከለ
የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያ ላይ የሚሸጥ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ነው፤
58. “Regulated Person”/ ‹‹ቁጥጥር የሚደረግበት ሰው›› ማለት በዚህ አዋጅ ወይም በሌላ አዋጅ መሠረት ፈቃድ የተሰጠው እና ባለስልጣኑ የስራ እንቅስቃሴውን በተመለከተ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመቆጣጠር ኃላፊነት ያለበት ሰው ወይም ፈቃድ የተሰጠው የሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ገበያ ወይም ፈቃድ ከተሰጠው የሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ገበያ ጋር ወይም ከባለፈቃድ ሰው ጋር የሚሰራ ማንኛውም ሰው ነው፤
59. “Repurchase Agreement”/ ‹‹ መልሶ የመግዛት ውል›› ማለት በተወሰነው ቀን በተወሰነ ዋጋ ወይም ባልተገለጸ
ወደ ፊት ባለ ቀን በተወሰነ ዋጋ ለመሸጥና በመቀጠልም መልሶ ለመግዛት የሚደረግ ውል ሲሆን ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮችን መሸጥንና መልሶ መግዛትን ወይም መግዛትንና መልሶ መሸጥን ያካትታል፤
60. “Rules”/ ‹‹ውስጠ-ደንቦች›› ማለት ከሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ፣ ከሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች አስቀማጭ እና ክፍያ አጣሪና ፈጻሚ ኩባንያ ወይም ራሱን በራሱ ከሚቆጣጠር ድርጅት
ጋር በተያያዘ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ፣ የሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች አስቀማጭ እና ክፍያ አጣሪና ፈጻሚ ኩባንያ፣ ወይም ራሱን በራሱ የሚቆጣጠር ድርጅት
እና የአባላቶቻቸዉ የገበያ እንቅስቃሴ እና የአሰራር ስነ-ምግባር የሚገዙባቸው ድንጋጌዎች ናቸው፤
61. “Secondary Market”/ ‹‹ሁለተኛ ደረጃ ገበያ›› ማለት ኢንቬስተሮች በመጀመሪያ ደረጃ ገበያ በቀጥታ ከአውጪው ወይም ከአገናኙ ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮችን ከሚገዙበት ውጪ አስቀድመው የወጡ ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮችን ከሌሎች ኢንቬስተሮች የሚገዙበት ገበያ ማለት ነው፤
62. “Securities”/ ‹‹ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች›› ማለት በማንኛውም ሕጋዊ መልክ ያለ
በገንዘባዊ ግብይት የድርሻ ባለቤትነትን የሚያረጋግጥ እና በባለስልጣኑ ፈቃድ መሠረት የሚተላለፍ ሆኖ የሚከተሉትን ያካትታል፡-
ሀ) በኩባንያ
ካፒታል ውስጥ የወጡ ወይም የሚወጡ አክሲዮኖችን፤
ለ) በኩባንያ የወጡ ወይም የሚወጡ ባለዕዳነትን የሚፈጥሩ ወይም የሚያረጋግጡ ማናቸውም ሰነድች፤
ሐ) ብድሮች፣
ቦንድች፣ እና ሌሎች ወደ ኩባንያ ካፒታልነት ሊቀየሩ የሚችሉ ሰነድችን፤
መ) ሁሉም
በመንግስት እና በመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ የወጡና ለግብይት የሚውሉ የህዝብ የብድር ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮች፤
ሠ) ማንኛውም
ከሰነደ ሙዓለ ንዋይ ጋር የተያያዘ እንደ
ኦፕሽን እና ለወደፊት የሚፈፀም ውል ዓይነቶች መብትን፣ ወይም ተዛማጅን፤
ረ) በጋራ
የኢንቨስትመንት ፈንድ ውስጥ ያለ የድርሻ ክፍልፋይን፤
ሰ) ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ሲባል ማንኛውም በባለስልጣኑ ሰነድ ነው ተብሎ የተፈረጀ ወረቀትን ወይም መሳሪያን ነገር
ግን እንደ ቼክ፣ የተስፋ ሰነድ፣ የሃዋላ ወረቀት፣ የንግድ ወረቀቶችን፣ ሌተር ኦፍ ክሬዲት፣ ጥሬ ገንዘብ
ማስተላለፍ እና በባንኮች መካከል እርስ በርስ
ብቻ የሚተላለፉ ሰነድችን፣ የመድን ፖሊሲዎችን፣
እና ለተጠቃሚዎች ከጡረታ ክፍያዎች የሚመነጩ መብቶችን
አያካትትም፡፡
63. “Securities Broker”/ ‹‹የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ደላላ›› ማለት ኮሚሽን እያስከፈለ በሌሎች ስም ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮችን የመሸጥ እና የመግዛት ስራ ላይ የተሰማራ ሰው ነው፤
64. “Securities Dealer”/ ‹‹የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ አከናዋኝ›› ማለት በሙሉ ጊዜው ወይም በትርፍ ጊዜው በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ
እንደ ወኪል፣ ደላላ፣ ወይም ራሱ ተገበያይ ሆኖ በሌላ አካል የወጡ ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮችን ለሽያጭ በማቅረብ፣ ለግዥ በማቅረብ ወይም በግብይት ስራ ላይ የተሰማራ ማንኛውም ሰው ነው፤
65. “Securities Depository and Clearing
Company”/ ‹‹የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች አስቀማጭ እና ክፍያ አጣሪና ፈጻሚ ኩባንያ›› ማለት ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮችን የማስቀመጥ፣ ክፍያዎችን የማጣራትና የመፈጸም እና ሌሎች ተያያዥ ተግባራትን የሚያከናውን ሕጋዊ ድርጅት ነው፤
66. “Securities Depository and
ClearingCompany Member”/ ‹‹የሰነድ ሙዓለ ንዋይ አስቀማጭ እና ክፍያ አጣሪ
ፈፃሚ ኩባንያ አባል›› ማለት የካፒታል ገበያ ተሳታፊ፣ ባንክ፣
በተውሶ ስም የሚሰራ፣ ወይም ሌላ የፋይናንስ ተቋም ሆኖ የሰነደ ሙዓለ
ንዋዮችን ግብይት ክፍያ ለማጣራትና ለመፈጸም የሚያስችል፣ ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች የሚቀበልበት፣ የሚይዝበት እና የሚያስተላልፍበት አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሂሳብ
መዝገብ በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች አስቀማጭ እና ክፍያ አጣሪና
ፈጻሚ ኩባንያ ያለው ነው፤
67. “Securities Exchange” / ‹‹የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ›› ማለት ፈቃድ ያላቸው የሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ገበያን የመስሪያ ቦታ በተመለከተ የገበያ መሰረተ-ልማቶችን አካትቶ የሚያቀርብ፣ የሚያዘጋጅ፣ የሚያመቻች ሲሆን በመሠረተ-ልማቱ አማካኝነት፡-
ሀ) የሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ሽያጭ፣ ግዥ እና ልውውጥ በቋሚነት የሚደረግበት፤
ለ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተቀባይነት እንዲያገኙ የታሰቡ ወይም በምክንያታዊነት የሚጠበቁ
ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለመሸጥ፣ ለመግዛት ወይም ለመለዋወጥ የሚደረጉ ጥሪዎች ወይም ግብዣዎች በቋሚነት የሚደረጉበት፤
ሐ) የተወሰኑ
ሰዎች፣ ወይም የተወሰነ መደብ ሰዎች ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮችን ለመሸጥ፣ ለመግዛት፣ ወይም ለመለዋወጥ ስለሚያቀረቡት ዋጋ ወይም በምክንያታዊነት ያቀርባሉ ተብሎ ስለሚጠበቅበት የሽያጭ ዋጋ፣ ወይም በልዋጭ ስለሚሰጡበት ዋጋ መረጃ በቋሚነት የሚሰጥበት ቦታ፤ ወይም
መ) በገበያው
ላይ ግብይት ስለተደረገባቸው ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮች ክፍያ የመፈጸም ስራ የሚሰራበት፤ ቦታ ነው፤
68. “Securities Lending”/ ‹‹ሰነደ ሙዓለ ንዋይን ማበደር›› ማለት ተመሳሳይ ቁጥር ያለውን ያንኑ ዓይነት ሰነደ ሙዓለ
ንዋይን ወደፊት ባለ
ቀን መልሶ ከማስረከብ ግዴታ ጋር በመልሶ የመግዛት ስምምነት እና በመሸጥና መልሶ በመግዛት ስምምነት ዓይነት በአጠቃላይ ጥሬ ገንዘብን
ወይም ቢያንስ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን ሌሎች ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮችን በዋስትና በማስያዝ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን በጊዜያዊነት መለዋወጥ ነው፤
69. “Securitization Transaction”/ ‹‹ለማይሸጡ ሰነድች የግብይት ሰነደ ሙዓለ ንዋይ መፍጠር›› ማለት ሀብትን ለአንድ ባለ
ልዩ ተልዕኮ ተቋም ለመሸጥ፣ ለማስተላለፍ ወይም በውሰት ለመስጠት መዘጋጀት ሲሆን ይህም፡-
ሀ) ለሽያጩ፣ ለማስተላለፉ ወይም ለምደባው ዋጋ የሚከፈለው በባለ ልዩ ተልዕኮ ተቋሙ ወይም በሌላ
ባለ ልዩ ተልዕኮ ተቋም በሚወጡ የዕዳ ሰነድች ወይም የዕዳ ሰነድ ክፍልፋዮች ሲሆን፣ እና
ለ) ለዕዳ ሰነድቹ ወይም ለዕዳ ሰነድ ክፍልፋዮቹ የሚከፈለው ክፍያ በዋናነት የሚገኘው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሀብቱን ከሚያስገኙት የገንዘብ ፍሰት ሲሆን
ነው፤
70. “Self-Regulatory Organization”/ ‹‹ራሱን በራሱ
የሚቆጣጠር ድርጅት›› ማለት የራሱን አባላቶች ፍትሃዊና ሀቀኛ
እንዲሆኑ እንዲሁም በካፒታል ገበያው ቀልጣፋ አሰራር እንዲሰፍን እና የኢንቬስተሮች እና የህብረተሰቡ ጥቅም እንዲከበር ለማድረግ አባላቱ እንዲከተሉ የሚገባቸውን የስነ-ምግባር ውስጠ-ደንቦች አውጥቶ በአባላቱ ቁጥጥር እንዲያደርግ በዚህ አዋጅ መሠረት እውቅና የተሰጠው ተቋም ነው፤
71. “Senior Personnel”/ ‹‹ከፍተኛ ባለሞያ›› ማለት ለቅጥሩ ወይም ለሹመቱ የባለስልጣኑ ስምምነት ወይም ቅደመ-ይሁንታ የሚያስፈልገው የባለፈቃድ ድርጅት ከፍተኛ የስራ አስፈጻሚ ወይም ሰራተኛ ነው፤
72. “Share”/ ‹‹አክሲዮን›› ማለት በአክሲዮን ኩባንያ ላይ ያለ
የባለቤትነት ጥቅም ወይም በጋራ የኢንቨስትመንት
ፈንድ ውስጥ ያለ የጥቅም ወይም የድርሻ መጠን ነው፤
73. “Special Purpose Institution”/ ‹‹ባለ ልዩ ተልዕኮ ተቋም›› ማለት፡-
ሀ) ለማንኛቸውም በሃብት የተደገፈ ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮች ባለቤቶች ለሆኑ ሰዎች የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሚያስገኙ ሀብቶችን እንደ
ባለቤት ወይም እንደ
አላባ ተጠቃሚ ለመያዝ፤ እና/ወይም
ለ) በሃብት የተደገፈ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለማውጣትና ለመሸጥ ብቻ የተቋቋመ ድርጅት ነው፤
74. “Subsidiary Company”/ ‹‹ተቀጥላ የሆነ ኩባንያ›› ማለት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሌላ ኩባንያ ባለቤትነት ወይም ቁጥጥር ስር ያለ
ኩባንያ ነው፤
75. “Underwriter”/ ‹‹በውክልና ሻጭ›› ማለት ማንኛውም አውጪው ያወጣቸውን ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮች በአውጪው ስም ለሽያጭ ለማቅረብ ወይም ለመሸጥ በማሰብ ከአውጪው የሚገዛ ወይም በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ
በውክልና የመሸጥ ተግባር ውስጥ የሚሳተፍ ወይም ተሳትፎ ያለው ሰው ነው፤
76. “Warrant”/ ‹‹የዋስትና ሰነድ›› ማለት ማንኛውም በዋስትና ሰነድ የተደገፈ ቢሆንም ባይሆንም አክሲዮኖችን ወይም የብድር ሰነደ
ሙዓለ ንዋዮችን ለመግዛት መብት የሚሰጥ ሰነድ ነው፤
77. “Person”/ ‹‹ሰው›› ማለት የተፈጥሮ ወይም የሕግ ሰውነት ያለው ሰው ማለት ነው፤
78. ማንኛውም በወንድ ጾታ የተቀመጠ አገላለጽ ሁሉ የሴትንም ጾታ ይጨምራል፡፡
79. ክፍል
ዘጠኝ፣ ጥቅምን ይፋ ስለማድረግ፣
አንቀፅ ፸፱(79). ትርጓሜ፡- ለዚህ ክፍል ዓላማ ‹‹ጥቅም ያለው ሰው››/“Interested
Person” ማለት ማንኛውም በግብይት የተመዘገበ
ኩባንያን ካፒታል አምስት (፭) በመቶ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆነውን በቀጥታ፣ በተዘዋዋሪ ወይም ከሌሎች ጋር በመጣመር ድርሻ ያለው ሰው ነው፡፡
አንቀፅ ፹፫ (83). ትርጓሜ፡- ለዚህ ክፍል አላማ
‹‹ለቁጥጥር የሚያበቃ የግዢ ጥያቄ››/ “acquisition offer” ማለት አንድን የተመዘገበ
ኩባንያ የዳይሬክተሮች ቦርድ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ
ለመቆጣጠር የሚያስችል የግዥ ጥያቄ ማቅረብ፣ ለመግዛት
ግፊት ማድረግ ወይም ከመቶኛ አብዛኛውን ባለቤት ለመሆን ጥያቄ ማቅረብ ነው፡፡

Comments
Post a Comment