Skip to main content

የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁ. 1141/2016 ማውጫ እና ትርጓሜ (Value Added Tax Proclamation 1141/2024)

 

የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁ. 1141/2016 ማውጫ እና ትርጓሜ

በኮድ መልክ ከተዘጋጁት አዋጆች በስተቀር በተወካዮች ምክር ቤት የሚወጡ አዋጆችም ሆኑ በሚንስትሮች ምክር ቤት የሚወጡ ደንቦች ማወጫ የላቸውም፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ 1341/2016 ም በረቂቅ ደረጃ ማውጫ የነበረው ቢሆንም አዋጁ ሲወጣ ግን እንደወትሮው ካለማውጫ ታትሟል፡፡ ይህም የህግ ባለሞያዎች እና ተማሪዎች ብሎም አዋጁን ለአንድ ለተወሰነ ጉዳይ ምላሽ ፍለጋ የሚመለከቱ ማናቸውም ሰዎች በቀላሉ የሚፈልጉትን የአዋጁ ወይም የደንቡ ክፍል ማግኘት እንዲቸግራቸው ሊያደርግ ይችላል፡፡ ይህ ለአዋጅ 1341/2016 የተዘጋጀ ማወጫ እና የቃላት ትረጓሜ ዝርዝር ለዚህ ችግር መፍትሄ ይሆናል በሚል የተቀናበረ ነው፡፡  የማውጫውን ፒዲኤፍ ይህን ሊንክ በመጫን ያገኙታል፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁ. 1141/2016 ማውጫ 

ክፍል አንድ፡ ጠቅላላ ድንጋጌዎች

1. አጭር ርዕስ

2. ትርጓሜ

3. የተፈጻሚነት ወሰን

4. የግብይት ዋጋ

5. በቀጥታ በገዢው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት

6. ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ

ፍል ሁለት ታክስ ስለመጣል እና ከታክስ ነፃ ስለማድረግ

7. የተጨማሪ እሴት ታክስ ስለመጣል

8. ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈፃሚ የሚሆንበት አቅርቦት

9. ከታክስ ነፃ የሆኑ አቅርቦቶች

10. ከታክሱ ነፃ የሆነ ወደአገር የሚገባ ዕቃ

11. በሌሎች ሕጐች የተቋቋሙ ከታክስ ነፃ የመሆን መብቶች ወይም ችሮታዎች ተፈፃሚት

የሌላቸው ስለመሆኑ፡፡

ክፍል ሦስት ስለመመዝገብ

12. የመመዝገብ ግዴታ

13. በፈቃደኝነት ስለመመዝገብ

14. የምዝገባ አፈፃፀም

15. የተመዘገበ ሰው ግዴታዎች

16. የተመዘገበ ሰው ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ ሲያቆም ስለሚሰጥ ማስታወቂያ

17. የመመዝገብ ግዴታን ከሚያስከትለው የገንዘብ መጠን በታች በመሆን ምክንያት

ስለሚቀርብ የምዝገባ ሥረዛ ማመልከቻ

18. ምዝገባው የተሰረዘበት ሰው ግዴታዎች

19. ምዝገባ በሚሠረዝበት ጊዜ እንደተከናወኑ ስለሚቆጠሩ ታክስ የሚከፈልባቸው አቅርቦቶች

ክፍል አራት አቅርቦትን የሚመለከቱ አጠቃላይ ድንጋጌዎች

20. ቅይጥ አቅርቦቶች

21. አቅርቦት ተከናወነ የሚባልበት ጊዜ

22. የአቅርቦት እሴት

23. በኢትዮጵያ የተከናወነ የዕቃ አቅርቦት

24. በኢትዮጵያ የተከናወነ የአገልግሎት አቅርቦት

25. በኤሌክትሮኒክ የማከፋፈያ ገበያ አማካኘነት ከሩቅ የሚከናወን የእቃ አቅርቦት

ክፍል አምስት ወደአገር ማስገባት

26. ዕቃ ወደአገር ገባ የሚባልበት ጊዜ

27. ወደአገር የገባ ዕቃ እሴት

28. ወደአገር በሚገቡ የካፒታል ዕቃዎች ላይ ሊከፈል የሚገባው የተጨማሪ እሴት ታክስ

እንዲዘገይ ስለማድረግ

ክፍል ስድስት ተቀናሽ የግብአት ታክስ

29. ተቀናሽ እንዲሆን የተፈቀደ የግብአት ታክስ

30. ተቀባይነት የሌለው የግብአት ታክስ ተቀናሽ

31. አዲስ የተመዘገበ ሰው የግብአት ታክስ ተቀናሽ

ክፍል ሰባት ልዩ ሁኔታዎች

32. ለራስ የሚደረግ አቅርቦት

33. ያገለገሉ ዕቃዎች አቅርቦት

34. የዕድል ሙከራ ጨዋታ አቅርቦት

35. ውርስ የተደረገ ዋስትና

36. የመብት፤የምርጫ እና የቫውቸር አቅርቦት

37. ቫውቸር እና ያልተገለጹ አቅርቦቶች

38. በቅድሚያ ክፍያ የሚቀርብ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት

39. የሠራተኞች ጥቅማ ጥቅም

40. አጠቃላይ መድን

41. በወኪሎች ወይም ለወኪሎች የተፈፀመ አቅርቦት

42. በባለገንዘብ የሚከናወን የዕቃ ሽያጭ

ክፍል ስምንት ማስተካከያ ስለማድረግ

43. የተከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ መጠን በማነሱ ምክንያት የሚደረግ ማስተካከያ

44. የተከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ በመብዛቱ ምክንያት የሚደረግ ማስተካከያ

45. ሊሰበሰብ ለማይችል ዕዳ ስለሚደረግ ማስተካከያ

46. መልሶ ሊሰበሰብ ከማይችል ዕዳ ውስጥ የተሰበሰበ ገንዘብ

ክፍል ዘጠኝ የተጨማሪ እሴት ታክስን የተጣራ ተከፋይ ሒሣብ ስለማሰላት

47. በአንድ የሒሣብ ጊዜ የተጣራ ተከፋይ የሚሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ

ክፍል አሥር ተመላሽ

48. በብልጫ የተከፈለን የግብአት ታክስ ወደፊት ስለማሸጋገር

49. ወደፊት ሳይሸጋገር ተመላሽ የሚደረግ በብልጫ የተከፈለ የግብአት ታክስ

50. ዘግይቶ በተከፈለ የተመላሽ ሒሣብ ላይ ስለሚከፈል ወለድ

51. ለዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች እና ለዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች የሚከፈል ተመላሽ ሒሣብ

ፍል አሥራ አንድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰነዶች

52. የታክስ ደረሰኞች                                        

53. የክሬዲት እና የዴቢት ሰነዶች

54. የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰነድ እንዲሰጥ ስለመጠየቅ

55. የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰነዶች አያያዝ

56. በወኪሎች አማካኝነት የተከናወኑ አቅርቦቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰነዶች

ክፍል አሥራ ሁለት የአስተዳደር እና የሥነ - ሥርዓት ደንቦች

57. የታክስ አስተዳደር አዋጅ ተፈፃሚነት

58. የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስታወቂያ

59. የተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈያ ጊዜ

60. ወደአገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ታክሱን ስለመሰብሰብ

61. ከአቅርቦቱ ተጠቃሚ ላይ ስለሚጠየቅ ታክስ

62. ከተከፋይ ሒሣብ ላይ የሚቀነስ የተጨማሪ እሴት ታክስ

63. የተወሰኑ ዕቃዎችን በመመዝገብ ረገድ ስለተጣለ ገደብ

64. የውጭ አገር አገልግሎት ሰጪ ግዴታዎች

65. በገዢው ታክስ በሚከፈልበት አቅርቦት ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ግዴታ ያለበት ሰው

ክፍል አሥራ ሦስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

66. ቅርንጫፎች እና የሥራ ክፍሎች

67. የተጨማሪ እሴት ታክስ የታከለበት ዋጋ

68. የተመዘገበ ሰው መሞት ወይም መክሰር እና ንብረት በመያዣነት የተቀበለ ሰው

69. የተጨማሪ እሴት ታክስ ያለመክፈል ዕቅድ

70. የገንዘብ ምንዛሪ

ክፍል አሥራ አራት የማጠቃለያ ድንጋጌዎች

71. ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን

72. የተሻሩ እና ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ሕጐች

73. የመሸጋገሪያ ድንጋጌ

74. አዋጁ ተፈፃሚ የሚሆንበት ቀን

አባሪዎች

አባሪ 1፡- አንቀጽ (9) ፡- ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ የሚሆንባቸው አቅርቦቶች

·         ክፍል ፩(1)፡- ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ዕቃዎች

·         ክፍል ፪ (2)፡- ለውጭ ሀገር የሚቀርቡ አገልግሎቶች

·         ክፍል ፫ (3)፡- ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ የሚደረግባቸው የሀገር ውስጥ አቅርቦቶች

·         ክፍል ፬ (4)፡- ትርጓሜ

አባሪ 2፡- አንቀጽ (10)፡- ከታክስ ነጻ የሆኑ አቅርቦቶ

አባሪ 3፡- አንቀጽ ፲፩ (11)፡- ከታክስ ነጻ የሆኑ ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎች

       

ትርጓሜ

በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ 1341/ 2016  ጥቅም ላይ የዋሉ እና በታክስ አስተዳደር አዋጅ ትርጓሜ የተሰጠባቸው ቃላት፣ በዚህ አዋጅ ሌላ ትርጉም ካልተሰጣቸው በስተቀር በታክስ አስተዳደር አዋጅ የተሰጣቸውን ትርጉም ይይዛሉ፡፡ በአዋጁ ጥቅም ላይ የዋሉ እና በአዋጁ ትርጉም የተሰጣቸው ቃላት የአዋጁ አንቀፅ 2 ላይ የሚገኙ ሲሆን እያዳንዱ ቃል በንዑስ አንቀፅ ትርጉም ተሰጥባት ከስር የተዘረዘሩት በየንዑስ አንቀፁ ስር ትርጉም የተሰጣቸው ቃላት ናቸው፡፡

ማስታወሻ፡- የአዋጁ አባሪ አንድ የራሱ በአባሪው ላይ የተካተቱ ቃላት ትርጓሜ ይዟል፡፡

 


1. Accounting Period”/ “የሒሣብ ጊዜ” ማለት ለት በቀን መቁጠሪያ ሰነድ የተመለከተው እያንዳንዱ ወር ነው፡፡ የነሐሴ እና የጳጉሜ ወራቶች በአንድነት ተጠቃለው እንደ አንድ ወር ይቆጠራሉ፤

 

2. “Adjustment Event” /‹‹ማስተካከያ የሚደረግበት ሁኔታ›› ማለት አንድን አቅርቦት በሚመለከት፡-

ሀ) አቅርቦቱ ሲሠረዝ፣

ለ) የአቅርቦቱ ሁኔታ መሠረታዊ ነው ሊባል በሚችል ደረጃ ሲቀየር ወይም ሲለወጥ፣

ሐ) የዋጋ ቅናሽ በመደረጉ ወይም በሌላ ማናቸውም ምክንያት ለአቅርቦቱ የሚፈጸመው ክፍያ ሲለወጥ፣ ወይም

መ) ለአቅራቢው የተፈጸመውን የዕቃ አቅርቦት በሚመለከት፤ የተሸጠው ዕቃ ወይም የዕቃው ከፊል ለአቅራቢው ሲመለስ ነው፡፡

3. “Administrative Penality”/ ‹‹አስተዳደራዊ መቀጫ›› ማለት በፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ፱፻፹፫/፪ሺ፰ (983/2016) ክፍል አሥራ አምስት ምዕራፍ ሁለት የተጣለው አስተዳደራዊ መቀጫ ነው፤

4. “Agent”/‹‹ወኪል›› ማለት አንድን ሰው በሚመለከት በዚህ ሰው ስም እና ትዕዛዝ የሚሠራ ማናቸውም ሰው ነው፤

5. “Capital Goods”/ ‹‹የካፒታል ዕቃ›› ማለት ማናቸውም ሰው ለሚያከናውነው ታክስ የሚከፈልበት የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ጥቅም ላይ የሚውል፣ ከአንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ ኤኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው እና ዕቃዎችን ለማምረት ወይም አገልግሎቶችን ለመስጠት የዋለ ዕቃ ሲሆን፣ ሆኖም የንግድ ዕቃዎችን አይጨምርም፤

6. “Commission”/ ‹‹ኮሚሽን›› ማለት የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር በመወሰኛ አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፷፫/፪ሺ፲፬ (1263/2021) የተቋቋመው የጉምሩክ ኮሚሽን ነው፤

7. “Consideration”/ ‹‹የግብይት ዋጋ›› ማለት ለዕቃና ለአገልግሎት የሚከፈለው ጠቅላላ ገንዘብ ሲሆን በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ (5) የተተረጎመውን ያካትታል፤

8. “Credit Note” /  ‹‹የክሬዲት ሰነድ›› ማለት የተመዘገበ ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶፫ (53) በተጣለበት ግዴታ መሠረት የሚሰጠው ሰነድ ነው፤

9. “Creditable Acquisition”/ ‹‹ተቀናሽ የሚሆን ግዥ›› ማለት የተመዘገበን ሰው በሚመለከት፡-

ሀ) በሌላ የተመዘገበ ሰው ለዚህ ሰው የተፈጸመ ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት፤

ለ) በቀጥታ በገዢው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት፤ ወይም

ሐ) ይህ ሰው ወደ ሀገር ያስገባው ዕቃ ነው፡፡

10. “Customs Legislation”/ ‹‹የጉምሩክ ሕግ›› ማለት፡-

ሀ) የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር ፰፻፶፱/፪ሺ፮ (859/2014) (እንደተሻሻለ)፣ እና

ለ) በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር ፰፻፶፱/፪ሺ፮ (859/2014) (እንደተሻሻለ) መሠረት የወጣ ማንኛውም ደንብ ወይም መመሪያ ነው፡፡

11.  “Debit Note”/  ‹‹የዴቢት ሰነድ›› ማለት የተመዘገበ ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶፫ (53) በተጣለበት ግዴታ መሠረት የሚሰጠው ሰነድ ነው፤

12. “Duty”/ ‹‹ቀረጥ›› ማለት በጉምሩክ ሕግ እና የዓለም አቀፍ የተዋሃደ የሸቀጦች አሰያየምና አመዳደብ ሥርዓትን ተከትሎ በወጣው የጉምሩክ የታሪፍ ደንብ መሠረት በገቢና ወጪ ዕቃዎች ላይ የሚጣልና የሚሰበሰብ ክፍያ ነው፤

13. “Electronic Distribution Platform”/  ‹‹የኤሌክትሮኒክ የማከፋፈያ ገበያ›› ማለት አቅራቢው በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ከሩቅ የሚሰጥ አገልግሎትን ወይም በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሚታዘዝን ዕቃ በማከፋፈያ መንገዱ አንቀሳቃሽ አማካኝነት ለሦስተኛ ወገን (ለተቀባዩ) የሚያቀርብበት ድረ-ገጽ፣ የኢንተርኔት ፖርታል፣ ጌትዌይ፣ በኤሌክትሮኒክ መንገድ ግብይት የሚፈጸምበት መደብር፣ የገበያ ቦታ፣ የማከፋፈያ መድረክ ወይም ሌላ ተመሳሳይ መንገድ ነው፤

14. “Electronically Ordered Goods”/ ‹‹በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሚታዘዝ ዕቃ›› ማለት በኤሌክትሮኒክ የመገናኛ ዘዴ የግዢ ትእዛዝ የተሰጠበት ዕቃ ነው፤

 

15. “Employee”/ ‹‹ተቀጣሪ›› ማለት ራሱን ችሎ የሚሰራን የስራ ተቋራጭ ሳይጨምር በሌላ ሰው መሪነትና ቁጥጥር ሥር ሆኖ አገልግሎት ለመስጠት በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት የተቀጠረ ግለሰብ ሲሆን የድርጅት ዳይሬክተርን ወይም በድርጅቱ አመራር ውስጥ ኃላፊነት የተሰጠውን ሌላ ሰው እንዲሁም ተሿሚንና የሕዝብ ተመራጭን ጨምሮ የመንግሥት የሥራ ኃላፊን ያጠቃልላል፤

16. “Employer”/ ‹‹ቀጣሪ›› ማለት ተቀጣሪን የቀጠረ ወይም ለተቀጣሪው ደመወዝ የሚከፍል ሰው ነው፤

17. “Exempt Import” / ‹‹ከታክሱ ነጻ የሆነ ወደ ሀገር የሚገባ ዕቃ›› ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፩ (11) በተደነገገው መሠረት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የተደረገና ከዚህ አዋጅ ጋር በተያያዘው ሠንጠረዥ ፫ (3) የተመለከተው ወደ ሀገር የሚገባ ዕቃ ነው፤

18. “Exempt Supply”/ ‹‹ከታክስ ነጻ የተደረገ አቅርቦት›› ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲ (10) በተደነገገው መሠረት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የተደረገና ከዚህ አዋጅ ጋር በተያያዘው ሠንጠረዥ ፪ (2) የተመለከተው አቅርቦት ነው፤

19.  “Finance Lease”/ ‹‹የፋይናንስ ኪራይ›› ማለት አከራዩ፡-

ሀ) ቀደም ሲል ይዞት የሚገኘውን የካፒታል ዕቃ፤ ወይም

ለ) በተከራዩ መራጭነት አቅራቢ ተብሎ ከሚጠራው ሦስተኛ ወገን የሚገዛውን የካፒታል ዕቃ፣ ተከራዩ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ የሚያልቅ በሁለቱ ወገኖች ስምምነት የተወሰነ ክፍያ በየተወሰነ ጊዜ በመፈጸም እንዲጠቀምበት የሚያከራይበት፣ የኪራይ ስምምነቱ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ አከራዩ በካፒታል ዕቃው ላይ ሙሉ የባለቤትነት መብት ይዞ የሚቆይበትና የኪራይ ዘመኑ ሲያበቃ ሁለቱም ወገኖች ከተስማሙ ተከራዩ የካፒታል ዕቃውን ሊገዛ የሚችልበት የኪራይ አይነት ነው፡፡

20. “Goods”/ ‹‹ዕቃ›› ማለት ግዙፋዊ ሀልዎት ያለው ማናቸውም የሚንቀሳቀስ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሆን፣ የሚከተሉትን አይጨምርም፡-

ሀ) ገንዘብን፣ ወይም

ለ) በገመድ፣ በኬብል፣ በሬዲዮ፣ በብርሃን ወይም በሌላ ማናቸውም የኤሌክትሮማግኔቲክ ዘዴ ወይም በተመሳሳይ ሌላ የቴክኒክ ዘዴ የሚተላለፍን ምርት፡፡

21. “Government Entity”/ ‹‹የመንግሥት ተቋም›› ማለት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በፌደራል ወይም በክልል መንግሥት ወይም በከተማ አስተዳደር በጀት የሚተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤት ነው፤

22. “Hire Purchase Agreement”/ ‹‹የዱቤ ግዢ ስምምነት›› ማለት አከራይና ተከራይ ባደረጉት ስምምነት መሰረት አከራይ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የሚደረግ ክፍያ እየተከፈለው አንድ የተወሰነ የካፒታል ዕቃን ተከራዩ እንዲጠቀምበት የሚፈቅድበት፣ እያንዳንዱ የኪራይ ክፍያ በተደረገ ቁጥር ለክፍያው ተመጣጣኝ በሆነ መቶኛ ልክ ለተከራዩ የባለቤትነት መብት የሚተላለፍበትና ተከራዩ የመጨረሻውን ክፍያ እንደፈጸመም በካፒታል ዕቃው ላይ ሙሉ የባለቤትነት መብት ወዲያውኑ የሚያገኝበት የኪራይ አይነት ነው፤

23.  “Import”/ ‹‹ወደ ሀገር ማስገባት›› ማለት ማናቸውንም ገቢ ዕቃ ወደ ጉምሩክ ክልል ማምጣት ወይም እንዲገባ ማድረግ ነው፤

24. “Importer”/ ‹‹አስመጪ›› ማለት እቃን ወደ ሀገር ከማስገባት ጋር በተያያዘ፤ የእቃው ባለቤት የሆነ ሰው ወይም እቃው ወደ ሀገር በሚገባበት ጊዜ በይዞታው ስር ያለ በእቃው ላይ ጥቅም ያለው ማናቸውም ሰው ነው፤

25.  “Inbound Tourism Product”/ ‹‹የሀገር ውስጥ ጥቅል የቱሪዝም አገልግሎት›› ማለት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰጥን የመኝታ፣ የምግብ፣ የትራንስፖርት፣ የጉብኝት ወይም ሌሎች የቱሪስት አገልግሎቶችን የሚጨምር አገልግሎት ነው፤

26. “Input Tax”/ ‹‹የግብዓት ታክስ›› ማለት የተመዘገበን ሰው በሚመለከት፡-

ሀ) ተቀናሽ የሚሆን ግዢ ላይ ሊከፈል የሚገባውን ማንኛውንም አስተዳደራዊ ቅጣት እና ወለድ ሳይጨምር ይህ ሰው ተቀናሽ የሚሆን ግዢ በሚፈጽምበት ጊዜ የከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ እና

ለ) ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም የተመዘገበው ሰው የግብአት ታክስ ሆኖ እንዲቆጠር የተወሰነ የገንዘብ መጠን ነው፡፡

27. “Input Tax Credit”/ ‹‹የግብአት ታክስ ተቀናሽ›› ማለት በግብአት ላይ የተከፈለና በዚህ አዋጅ ተቀናሽ እንዲሆን የተፈቀደ ታክስ ነው፤

28. “Large Unregistered Person”/ ‹‹ከፍተኛ ግብይት ያለው ያልተመዘገበ ሰው›› ማለት፡-

ሀ) ጠቅላላ ዓመታዊ የአቅርቦት መጠኑ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ (12) ንዑስ አንቀጽ ፪ (2) ከተመለከተው የገንዘብ መጠን በላይ የሆነ፤እና

ለ) ለታክሱ ያልተመዘገበ ሰው ወይም የመንግስት ተቋም ነው፡፡

29. “Money” / ‹‹ገንዘብ›› ማለት፡-

ሀ) በገንዘብ ቅርስ ሰብሳቢነት የተሰማሩ ከሚይዙት፣ በኢንቬስትመንት መልክ ከሚያዝ ወይም ሌሎች ስለገንዘብ የመመራመር ፍላጐት ባላቸው ከሚያዘው ውጪ ያለ በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም በሌላ ሀገር ሕጋዊ መገበያያ የሆነ ሣንቲም ወይም ወረቀት፤

ለ) የሀዋላ ወረቀት፣ የባንክ ድራፍት፣ የቃል ኪዳን ሰነድ፣ የፖስታ ቤት ሀዋላ ወይም የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ፤

ሐ) የገንዘብ ዋጋ ያለው እና መንግሥት ለሽያጭ  የሚያቀርበው ወይም የሚያወጣው እና በሕግ መሠረት የተጣሉ ክፍያዎችን ለመሰብሰብ የሚያገለግል ቴምብር፣ ቅጽ ወይም ካርድ፣ ወይም

መ) ክፍያን ለመፈጸም እንዲያገለግል የተሰጠ ማናቸውም፡-

(1) ክሬዲት ካርድ ወይም ዴቢት ካርድ፤ ወይም

(2) ማናቸውም ሰው በሚያንቀሳቅሰው የባንክ ሒሣብ ገቢ ወይም ወጪ በማድረግ የተከፈለ ክፍያ፡፡

30. “Output Tax” / ‹‹የውጤት ታክስ›› ማለት የተመዘገበን ሰው በሚመለከት፡-

ሀ) የተመዘገበ ሰው ከሚያከናውነው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ሊሰበስብ የሚችለው የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ እና

ለ) የተመዘገበ ሰው ላገኘው በቀጥታ በገዢው ታክስ ለሚከፈልበት አቅርቦት ሊከፍል የሚገባው የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ወይም

ሐ) ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም የተመዘገበው ሰው የውጤት ታክስ ሆኖ እንዲቆጠር የተወሰነ የገንዘብ መጠን ነው፡፡

 

31. “Prepaid Telecommunications Product”/ ‹‹አስቀድሞ ክፍያ የተፈጸመበት የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት›› ማለት የስልክ ካርድ፣ የቅድሚያ ክፍያ ካርድ፣ ሒሣብ የመሙያ ካርድ ወይም ማናቸውም ሌላ አስቀድሞ ክፍያ የተፈጸመበት የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሲሆን፣ በኤሌክትሮኒክ መንገድ የሚፈጸመውንም ይጨምራል፤

32. “Recipient”/ ‹‹ተቀባይ›› ማለት አቅርቦትን በሚመለከት አቅርቦቱ የተፈጸመለት ሰው ነው፤

33. “Registered Person”/ ‹‹የተመዘገበ ሰው›› ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ ወይም የመመዝገብ ግዴታ ያለበት ሰው ነው፤

34. “Registration Threshold”/ ‹‹የምዝገባ የገንዘብ መጠን›› በዚህ በአዋጅ አንቀጽ ፲፪ (12) ንዑስ አንቀጽ (፪) (2) የተመለከተው የምዝገባ የገንዘብ መጠን ነው፤

35. “Remote Services”/ ‹‹ከሩቅ የሚሰጥ አገልግሎት›› ማለት ከኢትዮጵያ ውጪ በሚገኝ የንግድ ስራ ቦታ ባለ አቅራቢ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኝ ተቀባይ የተሰጠ አገልግሎት ነው፤

36. “Reverse Charged Supply” / ‹‹በቀጥታ በገዢው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት›› ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ በተደነገገው መሠረት የአቅርቦቱ ተጠቃሚ ራሱ በቀጥታ ታክሱን የሚከፍልበት አቅርቦት ነው፤

37. “Services”/ ‹‹አገልግሎት›› ማለት ከዕቃ ወይም ከገንዘብ ውጪ የሆነ ማናቸውም ነገር ነው፤

38. “Supplier”/ ‹‹አቅራቢ›› ማለት አቅርቦትን በሚመለከት አቅርቦቱን የሚያከናውነው ሰው ነው፤

39. “Supply”/ ‹‹አቅርቦት›› ማለት የዕቃ አቅርቦት፣ የአገልግሎት አቅርቦት ወይም በቀጥታ በገዥው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ነው፤

40. “Supply of Services”/ ‹‹የዕቃ አቅርቦት›› ማለት፡-

ሀ) የዕቃ ሽያጭ፣ ልውውጥ ወይም የዕቃ ባለቤት የሆነ ሰው ዕቃውን በማስተላለፍ ረገድ ያለውን መብት በመጠቀም የሚያከናውነው ሌላ የማስተላለፍ ተግባር፤ ወይም

ለ) በዱቤ ግዥ ስምምነት ወይም በፋይናንስ ኪራይ ስምምነት አማካኝነት ዕቃዎችን በዱቤ የመግዛት ወይም የመከራየት ተግባር።

41. “Supply of Services”/ ‹‹የአገልግሎት አቅርቦት›› ማለት ከዕቃ ወይም ከገንዘብ አቅርቦት ውጪ ያለ ሌላ ማናቸውም ተግባር ሲሆን፣ የሚከተሉትን ይጨምራል፡-

ሀ) ማናቸውንም መብት መስጠት፣ ማስተላለፍ፣ ማቋረጥ ወይም መብት መጠቀምን መተው፤

ለ) የመገልገያ ቦታን ወይም ጥቅምን ለሌላ ማመቻቸት፤

ሐ) ማናቸውንም ሁኔታ መፍቀድ ወይም አንድን ድርጊት ከመፈጸም መታቀብ፤

መ) ከሙቀት ወይም ከኤሌክትሪክ የሚመነጭን ኃይል፣ ጋዝ ወይም ውሃ ማስተላለፍ ወይም ማቅረብ፤ ወይም

ሠ) አንድን ምርት በገመድ፣ በኬብል፣ በሬዲዮ፣ በብርሃን ወይም በሌላ የኤሌክትሮማግኔቲክ ዘዴ ወይም በተመሳሳይ የቴክኒክ ዘዴ ማስተላለፍ፡፡

42. “Tax Authority”/ ‹‹የታክስ ባለሥልጣን›› ማለት የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፷፫/፪ሺ፲፬ (1263/2021) የተቋቋመው የገቢዎች ሚኒስቴር ወይም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ መሠረት ታክሱን ለማስተዳደር በገቢዎች ሚኒስቴር ውክልና የተሰጠው የክልል መንግሥት ወይም የከተማ አስተዳደር ግብር ሰብሳቢ አካል ነው፤

43. “Tax Fraction”/ ‹‹የታክስ ክፍልፋይ›› ማለት ከዚህ በታች በተመለከተው ቀመር የሚከናወን የክፍልፋይ ስሌት ነው፡፡

ሀ/ (100 + ሀ)

ለዚህ ስሌት አፈጻጸም ‹‹ ሀ ›› ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ (፪)(ለ)/ 8(2)(ለ) መሠረት ተፈጻሚ የሚሆነው የተጨማሪ እሴት ታክስ መጣኔ ነው፡፡

44. “Tax Invoice”/ ‹‹የታክስ ደረሰኝ›› ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶፪ (52) በተጣለበት ግዴታ መሠረት የተመዘገበ ሰው የሚሰጠው ሰነድ ነው፤

45. “Taxable Activity” / ‹‹ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ›› የሚለው ሐረግ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ (7) የተሰጠውን ትርጉም ይይዛል፤

46. “Taxable Import”/ ‹‹ታክስ የሚከፈልበት ወደ ሀገር የሚገባ ዕቃ›› ማለት፡-

ሀ) ከታክሱ ነጻ ከሆነ፤ ወይም

ለ) የኤሌክትሮኒክ ገበያ አቅራቢ ወይም የኤሌክትሮኒክ የማከፋፈያ ገበያ ስራን የሚያከናውን የተመዘገበ ሰው ዕቃው ወደ ሀገር ከመግባቱ በፊት ከተጠቃሚው የተጨማሪ እሴት ታክስ ከሰበሰበበት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የታዘዘ ዕቃ፤ ውጪ ያለ ዕቃ ነው፡፡

47. “Taxable Supply”/ ‹‹ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት›› ማለት፡-

ሀ) ከታክስ ነጻ ከተደረገ አቅርቦት ውጪ ታክስ የሚከፈልበትን የሥራ እንቅስቃሴ በማከናወን ሂደት በኢትዮጵያ ውስጥ የተመረተ ዕቃ ወይም አገልግሎት አቅርቦት፤ ወይም

ለ) በዚህ አዋጅ ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት እንደሆነ የሚቆጠር አቅርቦት ነው፡፡

48. “Telecommunications Services”/ ‹‹የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት›› ማለት መልዕክት፣ ጽሁፍ፣ ስዕል፣ ድምጽ ወይም ማናቸውንም ሌላ መረጃ በገመድ፣ በሬዲዮ፣ በብርሃን፣ በኬብል ወይም በሌላ የኤሌክትሮማግኔቲክ ዘዴ ወይም በተመሳሳይ የቴክኒክ ዘዴ ማስተላለፍ፣ ማሠራጨት ወይም መቀበል ሲሆን፡-

ሀ) የማስተላለፍ፣ የማሠራጨት ወይም የመቀበል አቅምን የመጠቀም መብትን የማዘዋወር ወይም የማስተላለፍ፣ ወይም

ለ) ከዓለም አቀፍ ወይም ከሀገር አቀፍ የመረጃ መረብ ጋር የማገናኘት አገልግሎትን፣ ይጨምራል፡፡ ሆኖም የጽሑፍ፣ የስዕል፣ የድምጽ ወይም የመረጃ አቅርቦትን አይጨምርም፡፡

49. “Telecommunications Services Supplie”/ ‹‹የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ›› ማለት በኢትዮጵያ ወይም በሌላ ሀገር የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ የተሰጠው ሰው ነው፤

50. “Trading Stock” / ‹‹የንግድ ዕቃ›› ፡-

ሀ) ማንኛውም የተመረተ፣ የተፈበረከ፣ የተገዛ ወይም ለማምረት፣ ለመሸጥ ወይም ለመለወጥ በማናቸውም ሁኔታ የተገኘን ዕቃ፣

ለ) በማምረት ወይም በመፈብረክ ሂደት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል ማንኛውም ጥሬ ዕቃ ወይም አላቂ ዕቃ፣ ወይም

ሐ) ለጭነት ወይም ለሥራ የሚያገለግ እንስሳትን ሳይጨምር ማንኛውንም እንስሳ፣ ይጨምራል፡፡

51. “VAT”/ ‹‹የተጨማሪ እሴት ታክስ›› ማለት በዚህ አዋጅ የተጣለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ነው፤

52. “Voucher”/ ‹‹ቫውቸር›› ማለት በአምጪው ለእቃ ወይም ለአገልግሎት አቅርቦት ክፍያ ለመፈጸም ብቻ ሊውል የሚችል ቫውቸር፣ ቴምብር፣ ምትክ ሰነድ፣ ኩፓን ወይም ሌላ ተመሳሳይ ነገር ሲሆን፣ በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሚሰጡትን እና የቴሌኮሚኒኬሽን የቅድሚያ ክፍያ ካርድን ይጨምራል፣ ሆኖም የፓስታ ቴምብርን አይጨምርም፤

53.  “Zero-Rated Supply”/ ‹‹የዜሮ መጣኔ አቅርቦት›› በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ (9) በተደነገገው መሠረት ዜሮ መጣኔ ተፈጻሚ እንዲሆንበት የተደረገ ከዚህ አዋጅ ጋር በተያያዘው ሠንጠረዥ ፩/ አባሪ 1 የተመለከተ አቅርቦት ነው፤

54. በዚህ አዋጅ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ እና ትርጉም ያልተሰጣቸው ቃላትና ሐረጐች በታክስ አስተዳደር አዋጅ ትርጉም የተሰጣቸው ከሆነ በታክስ አስተዳደር አዋጁ የተሰጣቸው ትርጉም ይኖራቸዋል፤

55. በወንድ ጾታ የተገለጸ ማናቸውም ድንጋጌ የሴት ጾታንም ይጨምራል፤

56. “Person” / ‹‹ሰው›› ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፡፡


Comments