"In Claris non fit interpretatio." (When the text is clear, no interpretation is needed.) በጠበቃ ዘርአይ ወልደሰንበት መግቢያ፣ ይህ አጭር መነሻ የሆነ የሕግ ማስታወሻ በተሻሻለው የጸረ-ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3(1) ድንጋጌ ላይ የተደነገገውን በዋስትና የመፈታት መብት ገደብ ስፋትና ወሰን ዙርያ ያተኮረ ሲሆን፤ በተለይም በዚሁ ድንጋጌ ስር ስለተመለከተው የዋስትና መብት እና የዋስትና ክልከላ ከጅምሩ በተለያየ ምክንያት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ያልተያዙ ሰዎች፣ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ተይዘው በፖሊስ ወይም በፍርድ ቤት ዋስትና ከእስር ከተለቀቁ በኋላ በዚያው በተለቀቁበት ጉዳይ ላይ በሙስና ወንጀል የተከሰሱ ሰዎችና በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች ላይ የሚተገበርበትን ሕጋዊ ሁኔታ አስመልክቶ የውይይት በር ለመክፈት በማሰብ በዝርዝር የመጀመሪያ ምልከታና ዳሰሳ ለማድረግ ተሞክሯል። ይህንን የሕግ ማስታወሻ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ዋና ምክንያቶች በቅርቡ አንድ ደንበኛዬ የሆነ ሰው በሙስና ወንጀል ክስ የቀረበበት መሆኑን ከሌላ ሰው ከሰማ በኋላ ጉዳዩን አጣርቶ የሙስና ወንጀል ክሱ የቀረበበት የሙስና ወንጀል ችሎት ዘንድ ባልተያዘበትና ባልታሰረበት ሁኔታ ከውጭ በገዛ ፍቃዱ በቀረበ ጊዜ የጸረ ሙስና ወንጀል ችሎቱ የአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3(1) ድንጋጌን መሠረት በማድረግ በቂሊንጦ ማረፍያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል ሲል በቅርቡ የሰጠው የዋስትና ክልከላ ትእዛዝ/ውሳኔ፣ በዚህ ረገድም በፌደራል ፍርድ ቤቶች ዘንድ እንዲህ ዓይነት ክርክር ሲነሳ ጨርሶ ወይም እምብዛም የማይታይ በመሆኑ እና በዚህ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የሕግ ጽሁፍ...
Legathiopia
Legathiopia is a bilingual blog that documents the learning journey of a practicing attorney and host of the Legal Plus podcast. The blog features articles in both English and Amharic, focusing on the Ethiopian legal system and related fields. It serves as a platform for professional discourse, scholarly opinions, and intellectual analysis, aiming to enhance understanding of Ethiopia's legal environment.