Skip to main content

Posts

Showing posts from March, 2024

የፍትህ ሥርዓቱ ግብ ፍትህ ሣይሆን ሕግ እና ሥርዓት (law and order) ነው!

የፍትህ ሥርዓቱ ግብ ፍትህ ሣይሆን ሕግ እና ሥርዓት ነው የምለው ደስ እያለኝ ሳይሆን እያዘንኩ ነው፡፡ ይህን ጉዳይ ይበልጡን ባሰብኩት ቁጥር ፍትህ በሰው ልጅ እጅ አለፍ አለፍ እያለች ያጋጣሚ ልትገኝ ትችል ይሆናል እንጂ ትክክለኛ ፍትህ መስጠት ልዕለ ሰብ ሃይል ጣልቃ ገብነት ይፈልጋል፡፡ በሕግ ሞያ ባለሟልነት መስራት የራሱ ፈተናዎች፣ የራሱ ግራመጋባቶች (confusion and dilemma) አለው፡፡ አንዳንዴ የሕግ ሞያዬ ከሰው ልጅ ሁሉ ጋር በጅምላ ያጣላኛል፤ ፀቤ የማይታይ ነው፤ ልቦናዬ ውስጥ ነው፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ፀቤ ከራሴ ጋር ይሆናል፡፡ አንድ የህግ ባለሞያ በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ ያለውን ሚና ለመወጣት በሚያደርገው ጥረት ከራሱም ጋር ሳይቀር ይጣላል፡፡ ዳኛ፣ ጠበቃ፣ ነገረፈጅ ወይም ዐቃቤ ሕግ ሆኖ የተሰጠውን ሚና ለመወጣት ሲባትል ከራሴ ጋር ተጣልቼ አላውቅም የሚል ካለ ወይ ህሊናው መጅ አውጥቷል ካልሆነም የሰው ልጅ ድክመት ያልተጣባው የፍትህ ሥርዓቱን በተአምር የሚዘውር መልአክ ወይም ልቦናው ማመዛዘኑን የተነጠቀ አጋንንት ነው ስል መሞገቴ አይቀርም፡፡ ያለፈው ሰሞን አንድ ችሎት ውስጥ ነበርኩ፡፡ የተረጋጋ ባለጉዳዮችን በአክብሮት የሚያስተናግድ ሰብአዊነቱን በቀላሉ ልገነዘብለት የቻልኩት ዳኛ ተሰይሟል፡፡ ሦስት ጠበቆች እና አንድ ዐቃቤ ህግ ከፊቱ ቆመው ሙሉ ሰዓት ሊሞላ ጥቂት ለቀራቸው ደቂቃዎች የወከሉትን ወገን ፅድቅ ሲያገዝፉ የሌላኛውን ወገን ኃጢያት ሲያገኑ ቆዩ፡፡  ጉዳዩ የመኖሪያ ቤትን የተመለከተ የፍትሃብሄር ጉዳይ ነው፡፡ በክርክሩ ሂደት ከሣሽ የሆኑት ባልቴት ከጠበቃቸው ጀርባ ተቀምጠው፣ ወደ ምድር አቀርቅረው ድምፅ ሳያወጡ ያነበንባሉ፡፡ ፀሎት መስሎኝ ነበር፡፡ በኋላ ግን ደረቅ ፀሎት ሳይሆን በእንባ የረሰረሰ ምልጃ እንደሆነ ታዘብኩ፡፡ እኔም ተራዬ...