Skip to main content

Posts

Showing posts from December, 2024

“መዝገቡ አያሳይም!”

  በፍርድ ቤት የሚደረጉ ክርሮች እና የሚሰሙ ምሥክሮች በተለይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመቅረፀ ድምፅ ይያዛሉ፡፡ በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤቶች ግን አብዛኖቹ ክርከሮች እና የምስክሮች ቃል በዳኞች በእጅ ይፃፋል፡፡ በእነዚህ ችሎቶች ምሥክሮቻችሁ ያስረዱላችሁ ጭብጦች ሳይመዘገብላችሁ ቀርቶ ያውቃል? በመስቀለኛ ጥያቄያችሁ ያስጣላችሁት ነጥብ በፍርድ ቤት መዝገብ ውስጥ ሽታው ጠፍቶባችሁ ያውቅ ይሆን? በስር ፍርድ ቤት በምሥክሮች ስለመነገሩ እርግጠኛ የሆናችሁበትን ፍሬ ነገር ተመስርታችሁ ይግባኝ ጠይቃችሁ በይግባኝ ችሎቱ “እርሶ በምሥክሮች ተነግሯል ቢሉም ከስር ፍርድ ቤት መዝገብ የሚሉትን አያሳይም” ተብላችሁ ኩም ብላችሁ ታውቃላችሁ? እኔን ገጥሞኝ ያውቃል! ግን ለምን??? አንድ ጠበቃ ወዳጄ የገጠማትን አጫወተችኝ፡፡ በፍርድ ቤት መድረክ ግራ ቀኙ ምስክሮቻቸውን አቅርበው እየተፋለሙ ነው፡፡ የምተርከው ገጠመኝ የተፈጠረው የወዳጄ ባላጋራዎች   ምሥክር ቀርቦ በሚሰማበት ወቅት ነው፡፡ ምሥክሩ ባቀረበው ጠበቃ   ሲጠየቅ ቆይቷል፡፡ ምሥክሩን ያቀረበው ጠበቃ የሚጠይቀው የጥያቄ ዓይነት ዋና ጥያቄ ይባላል፤ በዋና ጥያቄ የሚቀርቡት ጥያቄዎች ምስክሩ የሚያስረዳውን ጉዳይ የመንገር ያህል እንዲሆኑ አይፈቀዱም፤ መሰል ጥያቄዎች መሪ ጥያቄ ይባላሉ፡፡ በተቃራኒው ደንበኛውን ወክሎ ምሥክሩን ያቀረበው ጠበቃ ዋና ጥያቄ አቅርቦ እንደጨረሰ ባላንጣው ጠበቃ የምስክሩን ቃል ተዓማኒነት ለማሳጣት ወይም ለማፍረስ ይጠይቃል፤ ይህ የጥያቄ ዓይነት መስቀለኛ ጥያቄ መጠሪያው ነው፡፡ በመስቀለኛ ጥያቄ ወቅት ምሥክሩን ያቀረበው ጠበቃ ከጠየቃቸው ወይም ምሥክሩ ካብራራው ርዕሰ ጉዳዮች ወይም ከእነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች ጋር በቀጥታ ከሚገናኙ ፍሬ ነገሮች ውጪ መጠየቅ አ...