Skip to main content

Posts

የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅን ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3(1) ድንጋጌ ዙሪያ የቀረበ መነሻ የሆነ አጭር የሕግ ማስታወሻ

"In Claris non fit interpretatio." (When the text is clear, no interpretation is needed.)   በጠበቃ ዘርአይ ወልደሰንበት መግቢያ፣ ይህ አጭር መነሻ የሆነ የሕግ ማስታወሻ በተሻሻለው የጸረ-ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3(1) ድንጋጌ ላይ የተደነገገውን በዋስትና የመፈታት መብት ገደብ ስፋትና ወሰን ዙርያ ያተኮረ ሲሆን፤ በተለይም በዚሁ ድንጋጌ ስር ስለተመለከተው የዋስትና መብት እና የዋስትና ክልከላ ከጅምሩ በተለያየ ምክንያት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ያልተያዙ ሰዎች፣ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ተይዘው በፖሊስ ወይም በፍርድ ቤት ዋስትና ከእስር ከተለቀቁ በኋላ በዚያው በተለቀቁበት ጉዳይ ላይ በሙስና ወንጀል የተከሰሱ ሰዎችና በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች ላይ የሚተገበርበትን ሕጋዊ ሁኔታ አስመልክቶ የውይይት በር ለመክፈት በማሰብ በዝርዝር የመጀመሪያ ምልከታና ዳሰሳ ለማድረግ ተሞክሯል። ይህንን የሕግ ማስታወሻ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ዋና ምክንያቶች በቅርቡ አንድ ደንበኛዬ የሆነ ሰው በሙስና ወንጀል ክስ የቀረበበት መሆኑን ከሌላ ሰው ከሰማ በኋላ ጉዳዩን አጣርቶ የሙስና ወንጀል ክሱ የቀረበበት የሙስና ወንጀል ችሎት ዘንድ ባልተያዘበትና ባልታሰረበት ሁኔታ ከውጭ በገዛ ፍቃዱ በቀረበ ጊዜ የጸረ ሙስና ወንጀል ችሎቱ የአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3(1) ድንጋጌን መሠረት በማድረግ በቂሊንጦ ማረፍያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል ሲል በቅርቡ የሰጠው የዋስትና ክልከላ ትእዛዝ/ውሳኔ፣ በዚህ ረገድም በፌደራል ፍርድ ቤቶች ዘንድ እንዲህ ዓይነት ክርክር ሲነሳ ጨርሶ ወይም እምብዛም የማይታይ በመሆኑ እና በዚህ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የሕግ ጽሁፍ...