Skip to main content

Posts

የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁ. 1141/2016 ማውጫ እና ትርጓሜ (Value Added Tax Proclamation 1141/2024)

  በኮድ መልክ ከተዘጋጁት አዋጆች በስተቀር በተወካዮች ምክር ቤት የሚወጡ አዋጆችም ሆኑ በሚንስትሮች ምክር ቤት የሚወጡ ደንቦች ማወጫ የላቸውም፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ 1341/2016 ም በረቂቅ ደረጃ ማውጫ የነበረው ቢሆንም አዋጁ ሲወጣ ግን እንደወትሮው ካለማውጫ ታትሟል፡፡ ይህም የህግ ባለሞያዎች እና ተማሪዎች ብሎም አዋጁን ለአንድ ለተወሰነ ጉዳይ ምላሽ ፍለጋ የሚመለከቱ ማናቸውም ሰዎች በቀላሉ የሚፈልጉትን የአዋጁ ወይም የደንቡ ክፍል ማግኘት እንዲቸግራቸው ሊያደርግ ይችላል፡፡ ይህ ለአዋጅ 1341/2016 የተዘጋጀ ማወጫ እና የቃላት ትረጓሜ ዝርዝር ለዚህ ችግር መፍትሄ ይሆናል በሚል የተቀናበረ ነው፡፡  የማውጫውን ፒዲኤፍ ይህን ሊንክ በመጫን ያገኙታል፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁ. 1141/2016 ማውጫ  ክፍል አንድ፡ ጠቅላላ ድንጋጌዎች 1. አጭር ርዕስ 2. ትርጓሜ 3. የተፈጻሚነት ወሰን 4. የግብይት ዋጋ 5. በቀጥታ በገዢው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት 6. ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ ክ ፍል ሁለት ታክስ ስለመጣል እና ከታክስ ነፃ ስለማድረግ 7. የተጨማሪ እሴት ታክስ ስለመጣል 8. ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈፃሚ የሚሆንበት አቅርቦት 9. ከታክስ ነፃ የሆኑ አቅርቦቶች 10. ከታክሱ ነፃ የሆነ ወደአገር የሚገባ ዕቃ 11. በሌሎች ሕጐች የተቋቋሙ ከታክስ ነፃ የመሆን መብቶች ወይም ችሮታዎች ተፈፃሚት የሌላቸው ስለመሆኑ፡፡ ክፍል ሦስት ስለመመዝገብ 12. የመመዝገብ ግዴታ 13. በፈቃደኝነት ስለመመዝገብ 14. የምዝገባ አፈፃፀም 15. የተመዘገበ ሰው ግዴታዎች 16. የተመዘገበ ሰው ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ ሲያቆም ስለሚሰጥ...

በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 የተካተቱ፣ በቀድሞው የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 ላይ የተደረጉ ለውጦች (The new Ethiopian VAT proclamation no. 1341/2024)

ዝግጅት:- ሀብታሙ ጥላሁን (የህግ አማካሪና ጠበቃ) መግቢያ የተጨማሪ እሴት ታክስ በዕቃ ወይም በአገልግሎት ፍጆታ ላይ የሚጣል ታክስ ሲሆን፤ በግብዓት ጥሬ ዕቃ (in put tax) ላይ የተከፈለን ታክስ በውጤት በምርት (out put tax) ላይ ከተሰበሰበ ታክስ በማቀናነስ ታክስ በታክስ ላይ እንዳይሰበሰብ (non-duble taxation) ማድረግ የሚያስችል ታክስ ነው፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ በሽያጭ ደረሰኝ ላይ የተመሠረተ ዘመናዊ የታክስ ሥርዓት በመሆኑ ታክስ ከፋዮች የማቀናነሱ ሥርዓት ተጠቃሚ ለመሆን ደረሰኝ ሊኖራቸው ስለሚገባ ደረሰኝ በመጠየቅ አንዱ ሌላውን እንዲቆጣጠሩ ተደርጎ የተቀረፀ ለታክስ አስተዳደር አመቺ የሆነ የታክስ ዓይነት ነው፡፡ ከዚህም በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ በፍጆታ ላይ የተጣለ በመሆኑ፤ ፍጃታን በመቀነስ፣ ቁጠባን የሚያበረታታ የታክስ ዓይነት ሲሆን፤ በካፒታል ዕቃዎች ላይ ተፈፃሚ ስለማይሆን ኢንቬስትመንትን የሚያበረታታ የታክስ አይነት ነው፡፡ በእነዚህ እና በሌሎችም ምክንያቶች በዓለማችን ከ170 በላይ የሆኑ አገሮች የተጨማሪ እሴት ታክስን ሥራ ላይ አውለዋል። ይህም በመሆኑ ኢንቬስተሮች ሀብታቸውን ሥራ ላይ ለማዋል ከአንዱ አገር ወደሌላው በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የተጨማሪ እሴት ታክስን ባህሪያት ጠንቅቀው ስለሚያውቁ በቀላሉ ለመግባባት ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ሲሆን፤ የሰዎች እና የዕቃዎች እንቅስቃሴ የተሳለጠ እንዲሆን አድርጓል፡፡ በአገራችንም የተጨማሪ እሴት ታክስ ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን፤ በአፈፃፀም በርካታ ችግሮች ያሉ ቢሆንም ከአገር ውስጥ ቀጥተኛ ያልሆኑ ታክሶች የሚሰበሰበው ገቢ መቶኛ በየጊዜው እየጨመረ እንዲሄድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ በ1994 ዓ.ም የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ከወጣ ወዲህ ...