Skip to main content

Posts

የፍትህ ሥርዓቱ ግብ ፍትህ ሣይሆን ሕግ እና ሥርዓት (law and order) ነው!

የፍትህ ሥርዓቱ ግብ ፍትህ ሣይሆን ሕግ እና ሥርዓት ነው የምለው ደስ እያለኝ ሳይሆን እያዘንኩ ነው፡፡ ይህን ጉዳይ ይበልጡን ባሰብኩት ቁጥር ፍትህ በሰው ልጅ እጅ አለፍ አለፍ እያለች ያጋጣሚ ልትገኝ ትችል ይሆናል እንጂ ትክክለኛ ፍትህ መስጠት ልዕለ ሰብ ሃይል ጣልቃ ገብነት ይፈልጋል፡፡ በሕግ ሞያ ባለሟልነት መስራት የራሱ ፈተናዎች፣ የራሱ ግራመጋባቶች (confusion and dilemma) አለው፡፡ አንዳንዴ የሕግ ሞያዬ ከሰው ልጅ ሁሉ ጋር በጅምላ ያጣላኛል፤ ፀቤ የማይታይ ነው፤ ልቦናዬ ውስጥ ነው፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ፀቤ ከራሴ ጋር ይሆናል፡፡ አንድ የህግ ባለሞያ በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ ያለውን ሚና ለመወጣት በሚያደርገው ጥረት ከራሱም ጋር ሳይቀር ይጣላል፡፡ ዳኛ፣ ጠበቃ፣ ነገረፈጅ ወይም ዐቃቤ ሕግ ሆኖ የተሰጠውን ሚና ለመወጣት ሲባትል ከራሴ ጋር ተጣልቼ አላውቅም የሚል ካለ ወይ ህሊናው መጅ አውጥቷል ካልሆነም የሰው ልጅ ድክመት ያልተጣባው የፍትህ ሥርዓቱን በተአምር የሚዘውር መልአክ ወይም ልቦናው ማመዛዘኑን የተነጠቀ አጋንንት ነው ስል መሞገቴ አይቀርም፡፡ ያለፈው ሰሞን አንድ ችሎት ውስጥ ነበርኩ፡፡ የተረጋጋ ባለጉዳዮችን በአክብሮት የሚያስተናግድ ሰብአዊነቱን በቀላሉ ልገነዘብለት የቻልኩት ዳኛ ተሰይሟል፡፡ ሦስት ጠበቆች እና አንድ ዐቃቤ ህግ ከፊቱ ቆመው ሙሉ ሰዓት ሊሞላ ጥቂት ለቀራቸው ደቂቃዎች የወከሉትን ወገን ፅድቅ ሲያገዝፉ የሌላኛውን ወገን ኃጢያት ሲያገኑ ቆዩ፡፡  ጉዳዩ የመኖሪያ ቤትን የተመለከተ የፍትሃብሄር ጉዳይ ነው፡፡ በክርክሩ ሂደት ከሣሽ የሆኑት ባልቴት ከጠበቃቸው ጀርባ ተቀምጠው፣ ወደ ምድር አቀርቅረው ድምፅ ሳያወጡ ያነበንባሉ፡፡ ፀሎት መስሎኝ ነበር፡፡ በኋላ ግን ደረቅ ፀሎት ሳይሆን በእንባ የረሰረሰ ምልጃ እንደሆነ ታዘብኩ፡፡ እኔም ተራዬ...

እርቦት የሰረቀ እና የገደለ፡ አስገዳጅ ሁኔታ? - የወንጀል ህጉ ሰብዓዊነትን ችላ ያለበት ድንጋጌው

  ረሃብ ክፉ ነው፡፡ ረሃብ አንጀትን ብቻ አይደለም የሚያጥፈው፡፡ አንገትን ያሳጥፋል፣ አስደፍቶ፡፡ ወዝን ያጠፋል፡፡ ግርማ ሞገስን ይነጥቃል፡፡ ረሃብ ክፉ ነው፡፡ ሰውየው የዚሁ የክፉው ረሃብ ምርኮኛ፣ የረሃብ ሰንሰለት እስረኛ ናቸው፡፡ ረሃብ አንጀታቸውን ብቻ አይደለም ያጠፉት አንገታቸውን ጭምር እንጂ፡፡ ግርማ ሞገሳቸውን ነጥቆ፣ ወዛቸውን መጦ ‹‹ረሃብተኛ›› አርጓቸዋል፡፡ ታዲያ ሌላ ምን ይባላላል፤ ረሃብ ስማቸውን ቀምቶ ‹‹ረሃብተኛ››፣ ‹‹ችግረኛ›› ወይም ፈረንጆቹ እንደሚሉት ‹ሆምለስ› (homeless) የተሰኙ አዳዲስ ስሞች አሰጣቸው፡፡ ይህ ሰው ኑሮ የተጫናቸውን፣ የሚቀምሱት ያጡትን ሁሉ ለማመልከት የተፈጠረ ተምሳሌታዊ ሰው አይደለም፡፡ አቶ ኦስትሪያቮቭ ተብሎ የሚጠራ ዩክሬናዊ ደም ያለው ጣልያን ውስጥ የሚኖር ነዳይ ነው፡፡ ታሪኩን የዘገበው ቢቢሲ ምን ያህል ቀናት ካለምግብ ያለፈቃዱ እንደፆመ ባይነግረንም መራብ ግን ተርቧል፡፡ እናም የታጠፈ አንጀቱን ለማላወስ ወደ አንዱ ሱፐርማርኬት ገባ እና ዳቦ፣ ሁለት ፍሬ አይብ እና የታሸገ ስጎ አንስቶ ለዳቦው ብቻ ከፍሎ ሊወጣ ሲል ጉዳዩን ሲያስተውል የነበረ ሌላ ተጠቃሚ   ለጥበቃዎች አሰታውቆ አስያዘው፡፡ ሳይከፍል ይዞት ሊወጣ የነበረው ቺዝ እና ስጎ 4.50 የሜሪካ ዶላር ዋጋ ያለው ነው፤ በኢትዮጵያ ገንዘብ      ብር ማለት ነው፡፡ እናም በፖሊስ እጅ ወደቀ፤ በ2011 እንደ ምዕራባውያን አቆጣጠር፡፡ በ2015 ዓ.ም (አሁንም በምዕራባውያን አቆጣጠር) ፍርድ ቤቱ (ለዚህች ጉዳይ እስከዛ የማንን ጎፈሬ ሲያበጥር እንደነበር እንጃ) ጥፋተኛ ብሎ ስድስት ወር እስራት እና 100 ይሮ የገንዘብ ቅጣት ወሰነበት፡፡ ርቦት የሰረቀ የመጀመሪያው ሰው አይደለም፡፡ እግዲያውስ የሱን...

አፈንጋጩ ህግ፡ የፍሬደሪክ ባስቲያት ዘ ሎው

  ፍሬደሪክ ባስቲያት መጣጥፉን ሲጀምር ህግ አፈንግጧል ይለናል፡፡ የህግ ተገቢ ቦታው እና አገልግሎቱን ያብራርናል፡፡ ቀጥሎም አፈንግጦ የት እንደደረሰ ያትታል፡፡ በሌላ አባባል የህግ ማፈንገጥ ከየት ወደ የት? ለምንስ? ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጠናል፡፡ መልካም ንባብ፡- ህግ አፈንግጧል! የመንግስት የፖሊስ ኃይልም አብሮ አፈንግጧል! እያልኩ ያለሁት ህግ ተገቢ አላማውን ስቷል ብቻ አይደለም፤ ከዓላማው ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ዓላማን እንዲከተል ተደርጓል ጭምር እንጂ! ህግ የሁሉም አይነት ስግብግብነት መሳሪያ ሆኗል! ወንጀልን መቆጣጠርን ትቶ ህግ እራሱ ሊቀጣቸው ይገቡ የነበሩ ጥፋቶች ወንጀለኛ ነው፡፡ ይህ እውነት ከሆነ፣ ከባድ እውነታ በመሆኑ   አቻዬ ዜጎችን ትኩረት ወደ እዚህ ጉዳይ እንድስብ ምግባር ግድ ይለኛል፡፡ ህይወት ከአምላክ የተሰጠ ስጦታ ነው ከአምላክ ሁሉን ነገር አጠቃሎ የያዘ ስጦታ ተቀብለናል፡፡ ይህ ስጦታ ህይወት ነው - አካላዊ፣ አእምሯዊ እና ምግባራዊ ህይወት፡፡ ሆኖም ህይወት ብቻውን ሊኖር አይችልም፡፡ የህይወት ፈጣሪ እንድንጠብቀው፣ እንድናዳብረው እና እንድናፈፅመው(ፍፅምናን እንድናለብሰው) ኃላፊነት ሰጥቶናል፡፡ ኃላፊነታችንን እንድንወጣ ደግሞ የአስደናቂ ችሎታዎች ስብስብ አቅርቦልናል፡፡ እንዲሁም በተለያዩ አይነት የተፈጥሮ ሃብቶች መሃል አስቀምጦናል፡፡ ችሎታዎቻችንን በመጠቀም እነዚህን የተፈጥሮ ሃብቶች ወደ ምርት ቀይረን እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ህይወት የታሰበላትን መንገድ እንድትጓዝ ይህ ሂደት አስፈላጊ ነው፡፡ ሰው ማለት ህይወት፣ ችሎታ እና ምርት፣ በሌላ አባባል ግለሰባዊነት፣ ነፃነት እና ንብረት ነው፡፡ ብልጣብልጥ የፖለቲካ መሪዎች ማታለያ ምንም ሆነ ምን ሶስቱ የአምላክ ስጦታዎች የትኛውንም ሰብዓዊ ህግ ይቀድማሉ፤ ደ...