Skip to main content

Posts

በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2014 አንዳንድ ድንጋጌዎች ላይ የቀረበ አጭር የመነሻ ሃሳብ ጽሁፍ

     በጠበቃ ዘርኣይ ወልደሰንበት 1. የፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2014 አንቀጽ 63(11) ድንጋጌ መሠረት የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣን የተሰጠው የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ የማውጣት ሥልጣን ነው? ወይንስ የማኅበሩን መመስረቻ ጽሁፍ የማውጣት ሥልጣን ነው? Article 63(11) of Federal Advocacy Service Licensing and Administration Proclamation No. 1249/2021 stipulated that the General Meeting shall have the power and duty to "Issue the Memorandum of Association of the Association amend and approve same." while its Amharic counterpart says that የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ "የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ ያወጣል፣ ያሻሽላል፣ ያጸድቃል፡፡" በማለት ደንግጓል፡፡  በዚህም መሠረት በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2014 አንቀጽ 63(11) ድንጋጌ የእንግሊዝኛው ቅጂ ላይ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የማኅበሩን መመስረቻ ጽሁፍ ያወጣል በሚል በግልጽ የተደነገገ ሲሆን የዚሁ አንቀጽ ድንጋጌ የአማርኛ ቅጂ በበኩሉ ደግሞ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ ያወጣል፡፡" በሚል በግልጽ ተደንግጓል፡፡ ከዚህም አንጻር፣ በአዋጁ አንቀጽ 63(11) ድንጋጌ የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቅጂዎች መካከል ግልጽ የሆነ መሰረታዊ ልዩነት ይገኛል፡፡ እንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ የሕግ አውጪው ትክክለኛ ሀሳብና ፍላጎት ምንም ይሁን ምን የአማርኛው ቅጂ ተፈጻሚነት ይኖረዋል ...

የፍትህ ሥርዓቱ ግብ ፍትህ ሣይሆን ሕግ እና ሥርዓት (law and order) ነው!

የፍትህ ሥርዓቱ ግብ ፍትህ ሣይሆን ሕግ እና ሥርዓት ነው የምለው ደስ እያለኝ ሳይሆን እያዘንኩ ነው፡፡ ይህን ጉዳይ ይበልጡን ባሰብኩት ቁጥር ፍትህ በሰው ልጅ እጅ አለፍ አለፍ እያለች ያጋጣሚ ልትገኝ ትችል ይሆናል እንጂ ትክክለኛ ፍትህ መስጠት ልዕለ ሰብ ሃይል ጣልቃ ገብነት ይፈልጋል፡፡ በሕግ ሞያ ባለሟልነት መስራት የራሱ ፈተናዎች፣ የራሱ ግራመጋባቶች (confusion and dilemma) አለው፡፡ አንዳንዴ የሕግ ሞያዬ ከሰው ልጅ ሁሉ ጋር በጅምላ ያጣላኛል፤ ፀቤ የማይታይ ነው፤ ልቦናዬ ውስጥ ነው፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ፀቤ ከራሴ ጋር ይሆናል፡፡ አንድ የህግ ባለሞያ በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ ያለውን ሚና ለመወጣት በሚያደርገው ጥረት ከራሱም ጋር ሳይቀር ይጣላል፡፡ ዳኛ፣ ጠበቃ፣ ነገረፈጅ ወይም ዐቃቤ ሕግ ሆኖ የተሰጠውን ሚና ለመወጣት ሲባትል ከራሴ ጋር ተጣልቼ አላውቅም የሚል ካለ ወይ ህሊናው መጅ አውጥቷል ካልሆነም የሰው ልጅ ድክመት ያልተጣባው የፍትህ ሥርዓቱን በተአምር የሚዘውር መልአክ ወይም ልቦናው ማመዛዘኑን የተነጠቀ አጋንንት ነው ስል መሞገቴ አይቀርም፡፡ ያለፈው ሰሞን አንድ ችሎት ውስጥ ነበርኩ፡፡ የተረጋጋ ባለጉዳዮችን በአክብሮት የሚያስተናግድ ሰብአዊነቱን በቀላሉ ልገነዘብለት የቻልኩት ዳኛ ተሰይሟል፡፡ ሦስት ጠበቆች እና አንድ ዐቃቤ ህግ ከፊቱ ቆመው ሙሉ ሰዓት ሊሞላ ጥቂት ለቀራቸው ደቂቃዎች የወከሉትን ወገን ፅድቅ ሲያገዝፉ የሌላኛውን ወገን ኃጢያት ሲያገኑ ቆዩ፡፡  ጉዳዩ የመኖሪያ ቤትን የተመለከተ የፍትሃብሄር ጉዳይ ነው፡፡ በክርክሩ ሂደት ከሣሽ የሆኑት ባልቴት ከጠበቃቸው ጀርባ ተቀምጠው፣ ወደ ምድር አቀርቅረው ድምፅ ሳያወጡ ያነበንባሉ፡፡ ፀሎት መስሎኝ ነበር፡፡ በኋላ ግን ደረቅ ፀሎት ሳይሆን በእንባ የረሰረሰ ምልጃ እንደሆነ ታዘብኩ፡፡ እኔም ተራዬ...

እርቦት የሰረቀ እና የገደለ፡ አስገዳጅ ሁኔታ? - የወንጀል ህጉ ሰብዓዊነትን ችላ ያለበት ድንጋጌው

  ረሃብ ክፉ ነው፡፡ ረሃብ አንጀትን ብቻ አይደለም የሚያጥፈው፡፡ አንገትን ያሳጥፋል፣ አስደፍቶ፡፡ ወዝን ያጠፋል፡፡ ግርማ ሞገስን ይነጥቃል፡፡ ረሃብ ክፉ ነው፡፡ ሰውየው የዚሁ የክፉው ረሃብ ምርኮኛ፣ የረሃብ ሰንሰለት እስረኛ ናቸው፡፡ ረሃብ አንጀታቸውን ብቻ አይደለም ያጠፉት አንገታቸውን ጭምር እንጂ፡፡ ግርማ ሞገሳቸውን ነጥቆ፣ ወዛቸውን መጦ ‹‹ረሃብተኛ›› አርጓቸዋል፡፡ ታዲያ ሌላ ምን ይባላላል፤ ረሃብ ስማቸውን ቀምቶ ‹‹ረሃብተኛ››፣ ‹‹ችግረኛ›› ወይም ፈረንጆቹ እንደሚሉት ‹ሆምለስ› (homeless) የተሰኙ አዳዲስ ስሞች አሰጣቸው፡፡ ይህ ሰው ኑሮ የተጫናቸውን፣ የሚቀምሱት ያጡትን ሁሉ ለማመልከት የተፈጠረ ተምሳሌታዊ ሰው አይደለም፡፡ አቶ ኦስትሪያቮቭ ተብሎ የሚጠራ ዩክሬናዊ ደም ያለው ጣልያን ውስጥ የሚኖር ነዳይ ነው፡፡ ታሪኩን የዘገበው ቢቢሲ ምን ያህል ቀናት ካለምግብ ያለፈቃዱ እንደፆመ ባይነግረንም መራብ ግን ተርቧል፡፡ እናም የታጠፈ አንጀቱን ለማላወስ ወደ አንዱ ሱፐርማርኬት ገባ እና ዳቦ፣ ሁለት ፍሬ አይብ እና የታሸገ ስጎ አንስቶ ለዳቦው ብቻ ከፍሎ ሊወጣ ሲል ጉዳዩን ሲያስተውል የነበረ ሌላ ተጠቃሚ   ለጥበቃዎች አሰታውቆ አስያዘው፡፡ ሳይከፍል ይዞት ሊወጣ የነበረው ቺዝ እና ስጎ 4.50 የሜሪካ ዶላር ዋጋ ያለው ነው፤ በኢትዮጵያ ገንዘብ      ብር ማለት ነው፡፡ እናም በፖሊስ እጅ ወደቀ፤ በ2011 እንደ ምዕራባውያን አቆጣጠር፡፡ በ2015 ዓ.ም (አሁንም በምዕራባውያን አቆጣጠር) ፍርድ ቤቱ (ለዚህች ጉዳይ እስከዛ የማንን ጎፈሬ ሲያበጥር እንደነበር እንጃ) ጥፋተኛ ብሎ ስድስት ወር እስራት እና 100 ይሮ የገንዘብ ቅጣት ወሰነበት፡፡ ርቦት የሰረቀ የመጀመሪያው ሰው አይደለም፡፡ እግዲያውስ የሱን...