በጠበቃ ዘርኣይ ወልደሰንበት 1. የፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2014 አንቀጽ 63(11) ድንጋጌ መሠረት የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣን የተሰጠው የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ የማውጣት ሥልጣን ነው? ወይንስ የማኅበሩን መመስረቻ ጽሁፍ የማውጣት ሥልጣን ነው? Article 63(11) of Federal Advocacy Service Licensing and Administration Proclamation No. 1249/2021 stipulated that the General Meeting shall have the power and duty to "Issue the Memorandum of Association of the Association amend and approve same." while its Amharic counterpart says that የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ "የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ ያወጣል፣ ያሻሽላል፣ ያጸድቃል፡፡" በማለት ደንግጓል፡፡ በዚህም መሠረት በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2014 አንቀጽ 63(11) ድንጋጌ የእንግሊዝኛው ቅጂ ላይ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የማኅበሩን መመስረቻ ጽሁፍ ያወጣል በሚል በግልጽ የተደነገገ ሲሆን የዚሁ አንቀጽ ድንጋጌ የአማርኛ ቅጂ በበኩሉ ደግሞ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ ያወጣል፡፡" በሚል በግልጽ ተደንግጓል፡፡ ከዚህም አንጻር፣ በአዋጁ አንቀጽ 63(11) ድንጋጌ የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቅጂዎች መካከል ግልጽ የሆነ መሰረታዊ ልዩነት ይገኛል፡፡ እንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ የሕግ አውጪው ትክክለኛ ሀሳብና ፍላጎት ምንም ይሁን ምን የአማርኛው ቅጂ ተፈጻሚነት ይኖረዋል ...
Legathiopia is a bilingual blog that documents the learning journey of a practicing attorney and host of the Legal Plus podcast. The blog features articles in both English and Amharic, focusing on the Ethiopian legal system and related fields. It serves as a platform for professional discourse, scholarly opinions, and intellectual analysis, aiming to enhance understanding of Ethiopia's legal environment.