Skip to main content

Posts

Showing posts from January, 2022

ሸሽተው የማያመልጡት፣ ውርስ

  “ሰው ከተወለደበት ቀን አንስቶ እስከ ሞተበት ቀን ድረስ የህግ መብት አለው፡፡” የፍትሃ ብሄር ህግ ቁጥር 1 አምስት መፅሃፍትን፣ 3367 ድንጋጌዎችን አካቷል፣ ሚያዚያ 27 ቀን 1952 ዓ.ም ታውጆ ከመስከረም 1 ቀን 1953 ጀምሮ ተፈፃሚ የተደረገው አብዛኛው ክፍሉ አሁንም ተፈፃሚ የሆነው የፍትሃ ብሄር ህጋችን በርካታ ህጎችን ያቀፈ የህጎች ስብስብ ነው፡፡ በውስጡ ከያዛቸው መካከል የውርስ ወይም የአወራረስ ህግ ይገኛል፡፡ በሁለተኛው መፅሃፍ አንቀፅ አምስት ውስጥ ከቁጥር 826 እስከ 1125 ድረስ ያሉት 299 ቁጥሮች የውርስ ጉዳይን የሚደነግጉ ናቸው፡፡   ውርስ ማናችንንም ሊያጋጥመን   የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ የውርስ ህግ ክፍል ባይሆንም ውርስ የተሰኘው ፅንሰ ሃሳብ እንዲኖር መግቢያዮ ላይ ያሰፈርኩት ድንጋጌ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ለዚህ ነው ብዙ ጊዜ የሃገራችን የህግ ምሁራን የውርስ ህግን ለማብራራት ሲነሱ ከዚህ ቀጥር የሚጀምሩት፡፡ የትኛውም ሰው ከተወለደበት ቀን ጀምሮ ባለመብት ነው፡፡ በተለያየ መልኩ የተለያዩ መብቶች እና ግዴታዎች ይኖሩታል፡፡ ሃገራችን የተቀበለቻቸው የተለያዩ ዓለም አቀፍ ህግጋትም መብቶችን ይሰጡታል፡፡ ከእነዚህም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-   UDHR (UNIVERSAL DECLARATION OF HUMAN RIGHTS) Article 17 1.    Everyone has the right to own property alone as well as in association with others.     በዚህ ድንጋጌ መሰረት የትኛውም ሰው ከሌሎችም ጋር ሆነ ለብቻው የራሱ ንብረት የማፍራት መብት አለው፡፡ ግን ንብረቱ ከየት ይመጣል? መልሱን ICESCR (INTERNATI...

ገድሎ መውረስ ይቻል ይሆን? (Is Killing to Inherit possible?)

  “No one shall be permitted to profit by his own fraud, or to take advantage of his own wrong, or to found any claim up on iniquity, or to acquire property by his own crime.”                      Riggs v palmer, New York court (1889) የጥንት ታሪክ ነው፤ግን በጣም ታዋቂ ታሪክ ነው፡፡ አሜሪካ ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ በ1882 (በእነሱው አቆጣጠር)ነው፡፡ ኤልመር የተባለ ግለሰብ አያቱን ገደላቸው፤ካለምንም ርእራሄ ምስኪኑን ሽማግሌ በመርዝ ገደላቸው፡፡ አያትየው ከዘመዶቻቸው ሁሉ የሚወዱት የልጅ ልጃቸው ነው መሰል አብዛኛውን ንብረታቸውን ለአቶ ኤልመር ነው የተናዘዙት፡፡አያቱ እስኪሞቱ መጠበቅ ሰልችቶት አይደለም የገደላቸው፤ተቀናቃኝ መጥቶበት እንጂ፡፡ እርጅና አጋርን መፈለግን እና ፍቅርን አይከለክልምና አያቱ ሚስት አገቡ፡፡ ልላ ተቀናቃኝ ተወዳጅ ሰው መምጣቱን ያስተዋለው ኤልመን የቀድሞውን ኑዛዜ አያቱ እንዳይቀይሩት ሰጋ፡፡ አሰበ፤ተጨነቀ፤ልያጣው የሜችለው ሃብት አይኑን አቀላው፤አንገበገበው፤አስገበገበው፡፡ አያቱን በመርዝ ገደላቸው፤ኑዛዜውን ሳይቀይሩ ሳይቀደም መቅደሙ ነው፡፡ለነገሩ እኮ ሰውየው ጭራሽ ኑዛዜያቸውንም ላይለውጡት ይችሉ ነበር፡፡   ከብዙ ምርመራና ክትትል በኋላ በድብቅ የሰራው ወንጀል ፀሃይ ሞቀው እና የኤልመር ወንጀል ተደረሰበት፤ፍርድ ቤት ቀረበ ከዛም ተፈረደበት፡፡አመታትንም በእስር ቤት አሳለፈ፤ፍርዱን ሲጨርስም ከእስር ተለቀቀ፡፡ይሄኔ አቶ ኤልመር...

ህግ ቦሌ ህዝብ ጉለሌ

   For the food by which we live, and for the law by which we live in peace, may Lord make us truly thankful. Ven Thomas Barfett, Lay Sheriff of London’s Chaplain July 1977   የህግ አስፈፃሚ መሆኑን ከስሙ መግለጫ መረዳት የምንችለው ይህ ግለሰብ ለአምላኩ ሲፀልይ ወይም የምስጋና ፀሎቱን እንዴት ብሎ እንደሚያቀርብ ሲገልፅ ነው “በህይወት እንቀጥል ዘንድ ምግብን እንዲሁም በሰላም እንኖርበት ዘንድ ህግን ስለሰጠን ጌታ ከልብ የተመሰገነ ይሁን” በማለት የተናገረው፡፡ ይህ ሰው ህግን ከምግብ ጋር አስተካሎታል፡፡ ደግሞም እውነታ አለው፤ የተረጋጋ ህይወት እንዲኖረን ህግ እና ስርአት የግድ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ለምን? ነጋድራስ ገብረ ህይወት ባይከዳኝ ተናገሩት ተብሎ የሚዘከርላቸው አባባል ወይም ብሂል ምላሹን የያዘ ይመስለኛል፡፡ እንዲህ አሉ፡- “በህግ ከማይኖር ትልቅ ባለብዙ ህዝብና ሠራዊት አገር፣ በህግና ሥርዓት የምትኖር ትንሽ ከተማ ቁም ነገር ትሰራለች፡፡” የህግ ምንነት ተመራማሪ የሆኑት ሮናልድ ዶርኪን Law’s Empire በተባለው መፃሃፋቸው መግቢያ ላይ ህግን ጥሩ አርገው ገልፀውታል፡፡ “We live in and by the law. It makes us what we are: citizens and employees and doctors and spouses and people who own things. It is sword, shield, and menace: we insist on our wage, or refuse to payout rent, or are forced to forfeit penalties, or are closed up in jail, all in the name ...

መወላወል/ indecision

  የበሽታዎች ሁሉ በሽታ፤        የስቃዮች በላይ ስቃይ ፤   የውስጥ ቃጠሎዎች ጌታ፤        የህሊና ግጭቶች አብይ፤ በገዛ አይንህ ክልል ስር፤        በህይወትህ መሃል ድንበር፤ የጉዞህ ውሉ መስመር፤        ሲጠፋህ ርቆ ሲቀበር፤ ቆርጦ ጉዞ ሲቸግር፤        ቆመህ ስትሮጥ፣ ተኝትህም ስትበር፤ ስትወላውል ለመወሰን ፤          ባለመወሰንህ ስትወስን፡፡ credit for picture: https://freesvg.org/silhouette-vector-clip-art-of-thinking-guy

የእስረኞች ዩኒፎርም ነገር እና የማልኮም ግላድዌል Blink – the power of thinking without thinking ነገር

  ማስታወሻ፡ ከተፃፈ የከረመ በወንጀል የተከሰሱ ሰዎች በችሎት ሲቀርቡ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች እስረኞቻቸውን ቢጫ ወይም ቀይ ዩኒፎርም አልብሰው ያቀርቧቸዋል፤ ወደ ፍርድ ቤቶች ያቀና ሰው ሁሉ የሚታዘበው እውነት ነው፡፡ መጀምሪያ ይህን ዩንፎርም የለበሱ እስረኞች ያየሁ ቀን ብዙም ደስ አላለኝም፤ ምን ማለት ነው? ሰው ሳይፈረድበት እንዴት “ወንጀለኛ ነኝ” የሚል መልዕክት የሚያስተላልፍ ባንዲራ አሸክሞ የማምጣት ያህል ባስቀያሚ ቢጫ ወይም ቀይ ዩኒፎርም ችሎት ላይ  ያቀርቧቸዋል? ስል ስብሰለሰል ትዝ ይለኛል፡፡    ስለ ምእራባውያን የወንጀል ችሎቶች አሰብኩ፤ ተከሳሹ ሱፉን ለብሶ ዘንጦ ነው የሚቀርበው፣ ራሱ እምቢኝ አልዘንጥም በቲሸርት እቀርባለሁ ካላለ በስተቀር፡፡ በእኛ ሃገርስ የወንጀል ችሎቶች ለምን እንደዚህ አይደረግም?… ወይ ሱፍ! ጭራሹኑ “ወንጀለኛ ነኝ” ዩኒፎርም አልብሰው ያቀርቧቸዋል፡፡  ማንም ሰው ሳይፈረድበት በፊት እንደወንጀለኛ ሊቆጠር እንደማይገባ የሚደነግገው ህገ መንግስታዊ እና ሰብዐዊ መብታዊ ነፃ ሁኖ የመገመት መብት መርህም በተደጋጋሚ ወደ አዕምሮ ይመላለሳል፡፡ ብዙም ሳልቆይ ግን ለራሴ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ጀመርኩ፡- ያው … ማለት … እ… እ … ባይሆን ጥሩ ነበር፡፡ ለችሎት ሲቀርቡ የራሳቸውን ልብስ ለብሰው ቢቀርቡ የተሻለ ነው፡፡ ግን … ቢለብሱም ያን ያህል ጉዳት የለውም፡፡ በምዕራቡ አለም (የኮመን ሎው የህግ ስርዓት በሚከተሉ አገሮች ) ወንጀለኛ ነው ወይስ አይደለም፣ ጥፋተኛ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ዳኝነት የሚሰጠው የህግ ትምህርት በሌላቸው እማኝ ዳኞች (ጁሪ) ነው፤ በመሆኑም አለባበስ ብሎም አጠቃላይ የተከሳሹ ገፅታ ተፅዕኖ ሊያሳድርባቸው ይችላል፡፡ በእኛ ሃገር ግን ፍርድ የሚሰጠው የህግ ትምህርት እ...